በኢትዮጵየ የዋጋ ግሽበት ከ30% ወደ 23% መቀነሱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይህን ያሉት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሲሰጡ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ዓመት መንግስት 529 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ባለፉት 11 ወራት 466 ቢሊየን ብር ገቢ እንደሰበሰበም አንስተዋል።
የተለያዩ ሀገራትን የግብር አሰባበሰብ ልምድ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከጂዲፒዋ 7% ብቻ ግብር እንደምትሰበስብ ተናግረዋል፡፡ ይህንን ቁጥር ወደ 10% ከፍ ማድረግ ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደሚረዳም አንስተዋል፡፡
የፋይናንስ ሴክተሩ በበርካታ አመላካቾች ጤናማ ሂደት ውስጥ ይገኛል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባንኮች ከሚያቀርቡት ብድር ከ80% በላይ የግሉ ዘርፍ ተጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡ ይህም የፋይናንስ ዘርፉ በጤናማ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን እንደሚያረጋግጥ ገልጸዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa/20240704/4897.html
በኢትዮጵየ የዋጋ ግሽበት ከ30% ወደ 23% መቀነሱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ
በኢትዮጵየ የዋጋ ግሽበት ከ30% ወደ 23% መቀነሱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ
Sputnik አፍሪካ
በኢትዮጵየ የዋጋ ግሽበት ከ30% ወደ 23% መቀነሱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይህን ያሉት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሲሰጡ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ... 04.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-04T15:59+0300
2024-07-04T15:59+0300
2024-07-04T16:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий