የማሊ መሪ በቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋች ሰይዱ ኬይታ የሚመራ የአግሮ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ በይፋ ከፈቱ

ሰብስክራይብ
የማሊ መሪ በቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋች ሰይዱ ኬይታ የሚመራ የአግሮ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ በይፋ ከፈቱ የማሊ ጊዜያዊ መሪ ማክሰኞ እለት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን ሪባን ቆርጠው በማሊ ሳንንኮሮባ ከተማ የሚገኘውን ተቋም ጎብኝተዋል። የሰይዱ ዲዮጎ አዋ አግሮ-ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ በሰባት ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው። ለምግብነት የሚውል የአትክልት ዘይት፣ የዘይት ኬክ እና የእንስሳት መኖ ማምረቻ፣ የሺአ ቅቤ ማምረቻ ክፍል፣ ሳሙና ማምረቻ ክፍል እና የፕላስቲክ ጣሳ ማምረቻ ክፍልን ጨምሮ ስድስት የኢንዱስትሪ ማምረቻ ክፍሎችን በአንድ ላይ የያዘ ነው። በ23 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት 400 የሚጠጋ ቋሚ የስራ እድል እንዲሁም ከ10,000 በላይ ቀጥተኛ ያልሆኑ ስራዎችን ይፈጥራል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0