የሀንጋሪ መሪ ኦርባን የዩክሬኑ ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር የተኩስ አቁም ማድረግን እንዲያጤኑ ጠየቁ
"ዘለንስኪን ሌላ አካሄድ እንዲያጤን ጠይቄዋለሀ፡ ፋታ ማድረግ፣ ተኩስ ማቆም እና ከዚያም ውይይቱን መቀጠል። ተኩስ ማቆም ውይይቱን ሊያፋጥን ይችላል" ሲሉ የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በኪዬቭ ከዩክሬኑ መሪ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ከተገናኙ በኋላ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ኦርባን ከዘለንስኪ ጋር ስላደረጉት ውይይት ሪፖርት አዘጋጅተው ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት እንደሚያቀርቡም ተናግረዋል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስዊዘርላንድ መፅሄት ዲ ዌልትዎቼ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዘለንስኪ ለመደራደር የተኩስ አቁም ማድረግ በሚለው ሃሳብ ላይ ጥርጣሬዎች እንዳሉት ተናግረዋል።
"አንዳንድ ጥርጣሬዎች አሉት። ጉዳዩ ላይ ብዙም ፍላጎት አላሳየም። እስቲ እናሰላስልበት፣ እናስብበት አለ። ከዚህ ቀደም በተደረጉ የተኩስ አቁም ስምምነቶች አንዳንድ መጥፎ ገጠመኞች አሉት፣ ይህም እንደሱ አመለካከት ለዩክሬን ጥሩ አልነበረም። ያለውን አቋም ተረድቷል፣ ገደቦቹን ገልጿል እና እንዴት መቀጠል እንደምንችል እናያለን ” ሲሉ ኦርባን ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa/20240703/4821.html
የሀንጋሪ መሪ ኦርባን የዩክሬኑ ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር የተኩስ አቁም ማድረግን እንዲያጤኑ ጠየቁ
የሀንጋሪ መሪ ኦርባን የዩክሬኑ ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር የተኩስ አቁም ማድረግን እንዲያጤኑ ጠየቁ
Sputnik አፍሪካ
የሀንጋሪ መሪ ኦርባን የዩክሬኑ ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር የተኩስ አቁም ማድረግን እንዲያጤኑ ጠየቁ "ዘለንስኪን ሌላ አካሄድ እንዲያጤን ጠይቄዋለሀ፡ ፋታ ማድረግ፣ ተኩስ ማቆም እና ከዚያም ውይይቱን መቀጠል። ተኩስ ማቆም ውይይቱን ሊያፋጥን ይችላል" ሲሉ... 03.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-03T15:12+0300
2024-07-03T15:12+0300
2024-07-03T15:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የሀንጋሪ መሪ ኦርባን የዩክሬኑ ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር የተኩስ አቁም ማድረግን እንዲያጤኑ ጠየቁ
15:12 03.07.2024 (የተሻሻለ: 15:40 03.07.2024)
ሰብስክራይብ