ሩሲያ 90 ምርኮኛ ወታደሮቿን ከዩክሬን ማስመለሷን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ 90 ምርኮኛ ወታደሮቿን ከዩክሬን ማስመለሷን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ "እ.አ.አ ሰኔ 25፣ 2024 ቀን በድርድሩ ሂደት መሰረት በእስር ላይ ሆነው የሞት አደጋ ላይ የነበሩ 90 የሩሲያ ወታደሮች የኪዬቭ አገዛዝ ከሚቆጣጠረው ግዛት ተለቀዋል። በምላሹም 90 የዩክሬን መከላከያ ኃይል የጦር ምርኮኞች ተዘዋውረዋል" ብሏል መግለጫው። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሩሲያ ወታደሮችን ከዩክሬን የማስመለሱ ሂደት ላይ የማደራደር ሚና እንደተጫወቱም የሚኒስቴሩ መግለጫ አክሏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0