ሩሲያ በብሪክስ ሀገራት የስፖርት ትብብር መርሃ ግብር ልታዘጋጅ መሆኑን የሩሲያ ስፖርት ሚኒስትር ገለፁ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ በብሪክስ ሀገራት የስፖርት ትብብር መርሃ ግብር ልታዘጋጅ መሆኑን የሩሲያ ስፖርት ሚኒስትር ገለፁ ሚካሄል ደግትያሬቭ እንዳሉት፤ይህ ሰነድ በስፖርት ዘርፍ በብሪክስ ሀገራት መካከል የትብብር ልማት እንዲኖር፤ የማይሸረሽሩ እሴቶች ለማጠናከር እንዲሁም የብሪክስ ስፖርት ጨዋታዎችን ለማካሄድ ሁኔታዎችንየሚያመቻች ነው። ሚኒስትሩ በተጨማሪም ሩሲያ በስፖርት መስክ ያለውን ግንኙነቶችን ለማዳበር ከብሪክስ ሀገራት አጋሮች ጋር የጋራ ትብብሮችን በማስፋት በፀረ-ዶፒንግ እርምጃዎች እና በሌሎች መስኮች ለማስተዋወቅ ሩሲያ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል። "ስፖርትን እንደ  መሳሪያ ለመጠቀም የሚደረጉ ሙከራዎችን በጋራ በመቃወም በሃገራዊ ወይም በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚደርሱ መድሎዎች ማስቆም አለብን" ሲሉም አክለዋል። መግለጫው የተነገረው በሩሲያ ካዛን ከተማ በተካሄደው የብሪክስ የስፖርት ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ነው። በውይይቱ ላይ ሚኒስትሮቹ ለብሪክስ ስፖርታዊ ጨዋታ ውድድሮች ስኬት እውቅና ሰጥተዋል፤ ከፍተኛ የውድድር እና አደረጃጀት ያለው እና በብሪክስ ሀገራት መካከል የሚደረግ አዲስ የስፖርት ዝግጅቶችን መፍጠር እንደሚያስፈልግ አረጋግጠዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0