የሰኔ 12 ቀትር ዋና ዋና የአለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የሰኔ 12 ቀትር ዋና ዋና የአለም ዜናዎች 🟠 ሩሲያ እና የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ በሁለቱ ሀገራት መካከል በኤሌክትሪክ ሃይል ዘርፍ እንዲሁም በሌሎች አዳዲስ የሀይል ማመንጫ ተቋማት፤ዲዛይንና ግንባታን ጨምሮ በትብብር ለመስራት መወያየታቸውን የሩሲያ ኢነርጂ ሚኒስቴር ዘግቧል። 🟠 ኮትዲቯር በባሌይን እና ካላኦ የባህር ዳርቻ የነዳጅ እና የተፈኖሮ ጋዝ ማግኘቷን ተከትሎ፤ የ በ 2027 ነዳጅና የጋዝ ምርቷ ከሶስት እጥፍ በላይ ሊሆን እንደሚችል ፕሬዝዳንት አላሳን ኦውታራ ተናግረዋል ። 🟠 የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በሩሲያ ቭላዲቮስቶክ ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የፓርቲዎች ጉባኤ "በብሪክስ አባል ሀገራት እና አጋር Uገራት" ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቀርጠኛ መሆኗን ገለፁ። 🟠 የናይጄሪያ የንግድ ዋና ከተማ ሌጎስ ባለስልጣናት የ15 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ “በጣም ኃይለኛ እና ተላላፊ” የኮሌራ በሽታ መከሰቱን ተከትሎ ለህብረተሰቡ  የጥንቃቄ መልእክት  አስተላልፈዋል። 🟠 በፑቲን እና በኪም ጆንግ ኡን መካከል ይፋዊ የስብሰባ መርሃ ግብር በፒዮንግያንግ ተካሄዷል። የሰሜን ኮሪያ መሪ ሩሲያ በዓለም ደረጃ  ስትራቴጅካዊ ሚዛን በመጠበቅ ረገድ ያላትን ሚና አንስተው፤በዩክሬን ለሚደረገው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ያላቸው ድጋፍ ሰጥተዋል። 🟠 በስዊዘርላንድ በተካሄደው የዩክሬን ኮንፈረንስ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ መሳተፍ ፤የድርጅቱን ቻርተር ይጥሳል ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩስያ ቋሚ መልእክተኛ  ቫሲሊ ኔቤንዛ ተናግረዋል። 🟠 የሩስያ ሰሜናዊ የባህር ሃይል የኒክሌር ሰርጓጅ መርከቦች በባረንትስ ባህር ላይ "ካሊብር" እና "ግራኒት" የሚሳኤል ተኩስ አደረጉ። 🟠 ትራምፕ በተመሰረቱባቸው አሳዛኝ ክሶች ዙሪያ በዊስኮንሲን ከሚገኙት ደጋፊዎች ጋር ከባይደን ጋር ከሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ክርክር በፊት አስተያየት ሰጥተዋል ። 🟠  በሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ ላይ አዲስ የሳንባ ነቀርሳ ክትባት በሩሲያ እንደሚሞከር የጋማሌያ የኢፒዲሚዮሎጂ እና የማይክሮባዮሎጂ ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሳንደር ጂንስበርግ አስታውቀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0