ሩስያ የሀገሪቱን ባንኮች የቅርንጫፍ ቢሮዎች አፍሪካ ውስጥ የመክፈት ፍላጎት እንዳላት፤ የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በ #SPIEF2024 አስታወቁ

ሰብስክራይብ
ሩስያ የሀገሪቱን ባንኮች የቅርንጫፍ ቢሮዎች አፍሪካ ውስጥ የመክፈት ፍላጎት እንዳላት፤ የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በ #SPIEF2024 አስታወቁ "ይህ በሩስያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ሀገራት ፍላጎት፣ ህጋዊ ሁኔታዎች እና ብሔራዊ የቁጥጥር ማዕቀፎች ላይ የተመሰረተ ነው" ብለዋል ማሪያ ዛካሮቫ። እንደ ቃል አቀባይዋ ገለጻ፣ ሩስያ ከአፍሪካ አጋሮች ጋር የሚደረጉ የንግድ እና የፋይናንስ ግብይቶች በማእከላዊ ባንኮች ለመፈፀም እና፤ በብሔራዊ መገበያያዎች ክፍያዎችን ለማከናወን የተለያዩ አማራጮችን ትመለከታለች። በተጨማሪም፤ ሀገሪቱ ቀጥተኛ ከባንክ-ባንክ የወኪል ግንኙነት ለመፍጠር እና፤ የውጭ ተጽእኖን የሚቋቋም የክፍያ መዋቅር በመገንባት ላይ መሆኗን ገልፀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0