ደቡብ ኮሪያ በሁለቱ በኮሪያዎች መካከል ያለውን ወታደራዊ ስምምነት ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል መተማመን መልሶ እስከመጣ ድረስ ማቋረጧን ዘገባዎች አመልክተዋል።

ሰብስክራይብ
ደቡብ ኮሪያ በሁለቱ በኮሪያዎች መካከል ያለውን ወታደራዊ ስምምነት ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል መተማመን መልሶ እስከመጣ ድረስ ማቋረጧን ዘገባዎች አመልክተዋል። የደቡብ ኮሪያ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ዛሬ ረፋድ ላይ ባደረገው ስብሰባ ፤እ.አ.አ አቆጣጠር በመስከረም 19 ቀን 2018 በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል የተደረገውን ወታደራዊ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ለማቆም የቀረበውን ሀሳብ ማክሰኞ በሚደረገው የመንግስት ስብሰባ ፤በአጀንዳነት ለማቅረብ ወስኗል። እ.ኤ.አ. በ 2018 በኮሪያ መካከል የተደረገው ወታደራዊ ስምምነት በረጅመንት ደረጃ የሚደረግ ወታደራዊ  እንቅስቃሴዎችን ወይም በድንበር አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች የሚደረጉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ማገዱ ይታወሳል። ሁለቱም ኮሪያዎች በ 2023 ያደርጉት ስምምነቱ ከፈራረሰ በኋላ በአከራካሪው ቢጫ ባህር አካባቢዎች ወታደራዊ ልምምድ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0