ቦትስዋና በላብራቶሪ የሚመረት አልማዝ ለኢኮኖሚዋ ስጋት እንደሆነ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ተናገሩ።

ሰብስክራይብ
ቦትስዋና በላብራቶሪ የሚመረት አልማዝ ለኢኮኖሚዋ ስጋት እንደሆነ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ተናገሩ። አልማዝ ከቦትስዋና ኢኮኖሚ በስተጀርባ ያለ አንቀሳቃሽ ኃይል ሲሆን፤ 40% የሚሆነው የመንግሥት ገቢ፣ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ምርት አንድ ሶስተኛውን እና 75 በመቶ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ይሸፍናል። ባለፈው አመት የቦትስዋና ታሪካዊ አጋር እና በሚያወጣቸው አልማዞች ዋጋ ከዓለም ቀዳሚ የአልማዝ አምራች የሆነው ዴ ቢርስ፤ ያልተነካ የአልማዝ ሽያጩ ከ6 ቢልየን ዶላር ወደ 3.6 ቢልየን ዶላር መቀነሱን፤ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0