https://amh.sputniknews.africa
በትግራይ ክልል 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 29፣ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለፀ
በትግራይ ክልል 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 29፣ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለፀ
Sputnik አፍሪካ
በትግራይ ክልል በኮቪድ 19 እና በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት ከ2012 ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ። 25.03.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-03-25T17:47+0300
2024-03-25T17:47+0300
2025-04-14T11:53+0300
африка общий
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/images/sharing/article/amh/980.jpg?1744620804
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በታቀደው ግዜ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተፈታኞች ምዝገባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር የፈተና ዝግጅት፣ የሎጅስቲክስና ሌሎችም ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል የአጠቃላይ ትምህርት ሁኔታ ወደ መደበኛ ሂደት መግባቱን መናገራቸው ይታወቃል።በዚህም በክልሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀት የተፋጠነ የትምህርት አሰጣጥ መተግበሩን ተናግረዋል።ፕሮፌሰር ብርሃኑ አክለውም ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ለዚህም መምህራንን እየጠሩ ነው ብለዋል።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በበኩሉ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ለፈተና የሚያበቃ የማጠናከሪያ ትምህርት እየወሰዱ ይገኛሉ ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።
африка общий
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2024
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
африка общий
በትግራይ ክልል 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 29፣ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለፀ
17:47 25.03.2024 (የተሻሻለ: 11:53 14.04.2025) የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ ከ
ኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በታቀደው ግዜ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተፈታኞች ምዝገባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር የፈተና ዝግጅት፣ የሎጅስቲክስና ሌሎችም ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል የአጠቃላይ ትምህርት ሁኔታ ወደ መደበኛ ሂደት መግባቱን መናገራቸው ይታወቃል።
በዚህም በክልሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀት የተፋጠነ የትምህርት አሰጣጥ መተግበሩን ተናግረዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ አክለውም ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ለዚህም መምህራንን እየጠሩ ነው ብለዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በበኩሉ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ለፈተና የሚያበቃ የማጠናከሪያ ትምህርት እየወሰዱ ይገኛሉ ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።