https://amh.sputniknews.africa
ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ በስድስት ከተሞች የባጃጅ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ጥሎት የነበረው ክልከላ አነሳ
ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ በስድስት ከተሞች የባጃጅ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ጥሎት የነበረው ክልከላ አነሳ
Sputnik አፍሪካ
የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ በባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ሸዋ ሮቢትና ላሊበላ ባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪዎች እንዳይንቀሳቁ ጥሎት የነበረውን ክልከላ ማንሳቱን አስታወቀ፡፡ 25.03.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-03-25T17:43+0300
2024-03-25T17:43+0300
2025-04-14T11:52+0300
африка общий
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/images/sharing/article/amh/833.jpg?1744620729
ዕዙ በከተሞቹ የባጃጅ ተሸከርካሪዎች እስከ ነሐሴ 17፣2015 ድረስ እንዳይንቀሳቀሱ ያደረገውን ክልከለ በመሻር ከነገ ነሐሴ 10 ቀን 2015፣ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ፈቅዷል፡፡ከዚህም ጋር በማያያዝ ክልከላዉ ከተነሣበት ጊዜ ጀምሮ የባጃጅ ባለቤቶችና አሽካርካሪዎች “የጽንፈኛ ቡድን” ሲል የጠራቸው አባላት፣ የዘረፉትን ንብረቶችና የትኛዉንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ከማጓጓዝ እንዲቆጠቡና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥብቅ ትዕዛዝ መስጠቱን ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ አስታውቋል፡፡ ይህንን ተላልፈዉ በተገኙት ላይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማሕቀፍ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድም አዟል፡፡የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ የፈጠረለትን ሰላማዊ ሁኔታ በመጠቀም አርሶ አደሩ ወደ መኸር አዝመራ ሥራዉ እየተመለሰ ነው ያለው የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ የግብርና ግብአቶችንም ወደ የአካባቢዎቹ ለማጓጓዝ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩን ዕዙ በግምገማው መገንዘቡን ገልጧል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናት በሚወሰዱ የማጥራት እርምጃዎች የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥብቅ መመሪያ መስጠቱም ተገልጧል፡፡የሁለተኛዉ ዙር ወታደራዊ ኦፕሬሽን ሥራዎች ከሞላ ጎደል እየተጠናቀቁ ነው ያለው ዕዙ ሕዝቡ ለመከላከያ ሠራዊታችን እያሳየ ያለው አቀባበል፣ የስንቅና የማበረታቻ ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን፣ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ሥራ እንዲጀምሩ ያለው ፍላጎትና እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን አመላክቷል፡፡
африка общий
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2024
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
африка общий
ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ በስድስት ከተሞች የባጃጅ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ጥሎት የነበረው ክልከላ አነሳ
17:43 25.03.2024 (የተሻሻለ: 11:52 14.04.2025) ዕዙ በከተሞቹ የባጃጅ ተሸከርካሪዎች እስከ ነሐሴ 17፣2015 ድረስ እንዳይንቀሳቀሱ ያደረገውን ክልከለ በመሻር ከነገ ነሐሴ 10 ቀን 2015፣ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ፈቅዷል፡፡ከዚህም ጋር በማያያዝ ክልከላዉ ከተነሣበት ጊዜ ጀምሮ የባጃጅ ባለቤቶችና አሽካርካሪዎች “የጽንፈኛ ቡድን” ሲል የጠራቸው አባላት፣ የዘረፉትን ንብረቶችና የትኛዉንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ከማጓጓዝ እንዲቆጠቡና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥብቅ ትዕዛዝ መስጠቱን ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ አስታውቋል፡፡ ይህንን ተላልፈዉ በተገኙት ላይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማሕቀፍ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድም አዟል፡፡የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ የፈጠረለትን ሰላማዊ ሁኔታ በመጠቀም አርሶ አደሩ ወደ መኸር አዝመራ ሥራዉ እየተመለሰ ነው ያለው የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ የግብርና ግብአቶችንም ወደ የአካባቢዎቹ ለማጓጓዝ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩን ዕዙ በግምገማው መገንዘቡን ገልጧል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናት በሚወሰዱ የማጥራት እርምጃዎች የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥብቅ መመሪያ መስጠቱም ተገልጧል፡፡የሁለተኛዉ ዙር ወታደራዊ ኦፕሬሽን ሥራዎች ከሞላ ጎደል እየተጠናቀቁ ነው ያለው ዕዙ ሕዝቡ ለመከላከያ ሠራዊታችን እያሳየ ያለው አቀባበል፣ የስንቅና የማበረታቻ ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን፣ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ሥራ እንዲጀምሩ ያለው ፍላጎትና እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን አመላክቷል፡፡