https://amh.sputniknews.africa
ጦርነትን ሸሽተን ጦርነት ውስጥ ገባን – በስደት በአማራ ክልል የሚኖሩ ሱዳናውያን
ጦርነትን ሸሽተን ጦርነት ውስጥ ገባን – በስደት በአማራ ክልል የሚኖሩ ሱዳናውያን
Sputnik አፍሪካ
በሀገራቸው የተከሰተውነ ጦርነት ሸሸተው ከ75 ሺ በላይ ሱዳናውያን ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያመላክታል። አብዘሃኛዎቹ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ሱዳናውያን ሰደተኞች ደግሞ በአማራ ክልል በኩል መሆኑን መረጃዎቹ ያሳያሉ። 25.03.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-03-25T17:37+0300
2024-03-25T17:37+0300
2025-04-14T11:50+0300
африка общий
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/images/sharing/article/amh/798.jpg?1744620649
ባለፉት ሳምንታት በአማራ ክልል ተከስቶ የነበረው ቀውስ ሱዳናውያኑን በከፍተኛ ሁኔታ እንዳስጨነቃቸው ዳባንጋ ሱዳን ለተሰኘ የሀገሪቱ ሚዲያ በሰጡት ቃለምልልስ ገልጸዋል፤ ከሞቀ ቤታቸው ሸሽተው ለስደት የዳረጋቸውን ጦርነት አሁን ደግሞ በስደት ተጠልለው ወደሚገኙበት የአማራ ክልል መምጣቱን በማስታወቅ።ጦርነትን ሸሽተን ጦርነት ውስጥ ገባን ሲሉ በአማራ ክልል በጎንደር እና በባህርዳር ከተማ የሚኖሩ ሱዳናውያን መናገራቸውን ያስነበበው የዳባንጋ ድረገጽ ከተሞቹን ጥለው ለሶስተኛ ስደት መዳረጋቸውን አስታውቋል፤ ወደ አዲስ አበባ ማቅናታቸውን ጠቁሟል።በርካታ ሱዳናውያን የአማራ ክልልን ለቀው ወደ አዲስ አበባ መጓዛቸውን ኑሮውን በባህርዳር አድርጎ የነበረው ኤልአጅሚ የተባለ ሱዳናዊ እንደገለጸለት ዘገባው አስታውቋል።በባህርዳር እና በጎንደር ይኖሩ የነበሩ ሱዳናውያን በከተሞቹ ተከስቶ በነበረው ቀውስ ሳቢያ ከፍተኛ ችግር እና መከራ ማሳለፋቸውን ሱዳናዊው ባክሪ አልአጅሚ እንደገለጸለት ያስነበበው ድረገጹ ለሳምንት ያክል መንገዶች መዘጋታቸው፣ ምግብ ቤቶች እና ሲቆች አለመከፈታቸው የመከራ ቀናት እንድናሳልፍ አድርጎናል ማለቱንም አካቷል።የኢትዮጵያ መንግስት የመኖሪያ ቪዛቸውን ለማደስ በየወሩ 80 ዶላር እንድንከፍል ያስገድደናል ሲሉ ከችግር ላይ ችግር በማስተናገድ ላይ ነን ሲል ሱዳናዊው ባካሪ መናገሩን ያስነበበው ድረገጹ በክልሉ ቀውስ ከመከሰቱ በፊት የቪዛ ማደሻ ክፍያውን እንዲያስቀርላቸው ለክልሉ መንግስት ጠይቀው እንደነበር መግለጹን አስታውቋል።ሱዳናውያኑ የኢትዮጵያን ድነበር አቋርጠው ሲገቡ ሁለት አማራጭ እንደሚቀርብላቸው ያመላከተው የድረገጹ ዘገባ ወደ መጠለያ ካምፕ መግባት የሚፈልጉ ሱዳናውያን ምንም አይነት የቪዛም ሆነ ሌላ ክፍያ እንደማይጠየቁ ጠቁሟል።
африка общий
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2024
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
африка общий
ጦርነትን ሸሽተን ጦርነት ውስጥ ገባን – በስደት በአማራ ክልል የሚኖሩ ሱዳናውያን
17:37 25.03.2024 (የተሻሻለ: 11:50 14.04.2025) ባለፉት ሳምንታት በአማራ ክልል ተከስቶ የነበረው ቀውስ ሱዳናውያኑን በከፍተኛ ሁኔታ እንዳስጨነቃቸው
ዳባንጋ ሱዳን ለተሰኘ የሀገሪቱ ሚዲያ በሰጡት ቃለምልልስ ገልጸዋል፤ ከሞቀ ቤታቸው ሸሽተው ለስደት የዳረጋቸውን ጦርነት አሁን ደግሞ በስደት ተጠልለው ወደሚገኙበት የአማራ ክልል መምጣቱን በማስታወቅ።ጦርነትን ሸሽተን ጦርነት ውስጥ ገባን ሲሉ በአማራ ክልል በጎንደር እና በባህርዳር ከተማ የሚኖሩ ሱዳናውያን መናገራቸውን ያስነበበው የዳባንጋ ድረገጽ ከተሞቹን ጥለው ለሶስተኛ ስደት መዳረጋቸውን አስታውቋል፤ ወደ አዲስ አበባ ማቅናታቸውን ጠቁሟል።በርካታ ሱዳናውያን የአማራ ክልልን ለቀው ወደ አዲስ አበባ መጓዛቸውን ኑሮውን በባህርዳር አድርጎ የነበረው ኤልአጅሚ የተባለ ሱዳናዊ እንደገለጸለት ዘገባው አስታውቋል።በባህርዳር እና በጎንደር ይኖሩ የነበሩ ሱዳናውያን በከተሞቹ ተከስቶ በነበረው ቀውስ ሳቢያ ከፍተኛ ችግር እና መከራ ማሳለፋቸውን ሱዳናዊው ባክሪ አልአጅሚ እንደገለጸለት ያስነበበው ድረገጹ ለሳምንት ያክል መንገዶች መዘጋታቸው፣ ምግብ ቤቶች እና ሲቆች አለመከፈታቸው የመከራ ቀናት እንድናሳልፍ አድርጎናል ማለቱንም አካቷል።የኢትዮጵያ መንግስት የመኖሪያ ቪዛቸውን ለማደስ በየወሩ 80 ዶላር እንድንከፍል ያስገድደናል ሲሉ ከችግር ላይ ችግር በማስተናገድ ላይ ነን ሲል ሱዳናዊው ባካሪ መናገሩን ያስነበበው ድረገጹ በክልሉ ቀውስ ከመከሰቱ በፊት የቪዛ ማደሻ ክፍያውን እንዲያስቀርላቸው ለክልሉ መንግስት ጠይቀው እንደነበር መግለጹን አስታውቋል።ሱዳናውያኑ የኢትዮጵያን ድነበር አቋርጠው ሲገቡ ሁለት አማራጭ እንደሚቀርብላቸው ያመላከተው የድረገጹ ዘገባ ወደ መጠለያ ካምፕ መግባት የሚፈልጉ ሱዳናውያን ምንም አይነት የቪዛም ሆነ ሌላ ክፍያ እንደማይጠየቁ ጠቁሟል።