https://amh.sputniknews.africa
የተባበሩት አረብ ኤሚሬት ፕሬዝዳንት ሸክ መሃመድ ቢን ዛይድ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
የተባበሩት አረብ ኤሚሬት ፕሬዝዳንት ሸክ መሃመድ ቢን ዛይድ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
Sputnik አፍሪካ
የተባበሩት አረብ ኤሚሬት ፕሬዝዳንት እና የአቡዲያቢ ገዢ ሸክ መሃመድ ቢን ዛይድ ለይፋዊ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት ነሃሴ 12/ 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ገቡ። 25.03.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-03-25T17:22+0300
2024-03-25T17:22+0300
2025-04-14T11:49+0300
африка общий
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/images/sharing/article/amh/637.jpg?1744620581
አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስለጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ውድ ወንድሜ እና ጓደኛዬ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣህ።እያደገ የመጣው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በመከባበር እና ለጋራ እድገት የጋራ ራዕይ ላይ የተመሰረተ ነው። ዘላቂ ልማትን ለማስቀጠል ትብብራችንን እንቀጥላለን” ሲሉ መልዕክታቸውን ስተላልፈዋል፡፡ሼክ ቢን ዛይደ በኢትዮጵያ ለመጨረሻ ግዜ ጉብኝት ያደረጉት በ2011 ዓ.ም ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብየ አህመድ ወደ ስልጣን በመጡ ከወራት በኋላ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ ሸክ ቢን ዛይድ የዩናይትድ አረብ ኤሚሬት ልዑል አልጋወራሽ በነበሩበት ወቅት ሲሆን በጉብኝታቸው ወቅትም የሶስት ቢሊየን ዶላር እርዳታ እና ብድር መስጠታቸው ይታወቃል።ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሸክ ቢን ዛይድ የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል።ለጉዳዩ ቅርበት ያለው የአዲስ ስታንዳርድ የዲፕሎማቲክ ምንጮች እደገለፁት ምናልባትም ለኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግን ጨምሮ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ኢትዮጵያ በርካታ ስምምነቶችን ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በዚህ አመት ጥር ወር ላይ በአረብ ኤምሬትስ ባደረጉት ጉብኝት ሁለቱ ሀገራት በኢትዮጵያ እስከ 2000 ሜጋ ዋት ሊደርስ የሚችል 500 ሜጋ ዋት ኃይል ያላቸውን የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለማልማት ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።ከዛ ቀደም ብሎ ከአንድ አመት በፊት ጥር ወር ላይ ጠ/ሚ አብይ አህመድ እና የውጭ ጉዳይና የመከላከያ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ልዑካን ቡድናቸው በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጎብኝት ባደረጉበት ወቅት በሸክ መሃመድ ቢን ዛይድ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
африка общий
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2024
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
африка общий
የተባበሩት አረብ ኤሚሬት ፕሬዝዳንት ሸክ መሃመድ ቢን ዛይድ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
17:22 25.03.2024 (የተሻሻለ: 11:49 14.04.2025) አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስለጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ውድ ወንድሜ እና ጓደኛዬ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣህ።እያደገ የመጣው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በመከባበር እና ለጋራ እድገት የጋራ ራዕይ ላይ የተመሰረተ ነው። ዘላቂ ልማትን ለማስቀጠል ትብብራችንን እንቀጥላለን” ሲሉ መልዕክታቸውን ስተላልፈዋል፡፡ሼክ ቢን ዛይደ በኢትዮጵያ ለመጨረሻ ግዜ ጉብኝት ያደረጉት በ2011 ዓ.ም ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብየ አህመድ ወደ ስልጣን በመጡ ከወራት በኋላ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ ሸክ ቢን ዛይድ የዩናይትድ አረብ ኤሚሬት ልዑል አልጋወራሽ በነበሩበት ወቅት ሲሆን በጉብኝታቸው ወቅትም የሶስት ቢሊየን ዶላር እርዳታ እና ብድር መስጠታቸው ይታወቃል።ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሸክ ቢን ዛይድ የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል።ለጉዳዩ ቅርበት ያለው የአዲስ ስታንዳርድ የዲፕሎማቲክ ምንጮች እደገለፁት ምናልባትም ለኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግን ጨምሮ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ኢትዮጵያ በርካታ ስምምነቶችን ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በዚህ አመት ጥር ወር ላይ በአረብ ኤምሬትስ ባደረጉት ጉብኝት ሁለቱ ሀገራት በኢትዮጵያ እስከ 2000 ሜጋ ዋት ሊደርስ የሚችል 500 ሜጋ ዋት ኃይል ያላቸውን የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለማልማት ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።ከዛ ቀደም ብሎ ከአንድ አመት በፊት ጥር ወር ላይ ጠ/ሚ አብይ አህመድ እና የውጭ ጉዳይና የመከላከያ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ልዑካን ቡድናቸው በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጎብኝት ባደረጉበት ወቅት በሸክ መሃመድ ቢን ዛይድ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡