https://amh.sputniknews.africa
በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ዙሪያ ዘገባ በመስራታቸው የታሰሩ ጋዜጠኞችን መንግስት
በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ዙሪያ ዘገባ በመስራታቸው የታሰሩ ጋዜጠኞችን መንግስት
Sputnik አፍሪካ
በአማራ ክልል ስላለው ወቅታዊ ውጥረት ዘገባ በመስራታቸው የታሰሩ 11 ጋዜጠኞችን መንግስት እንዲፈታ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የተሰኘው የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ጠየቀ፡፡ 25.03.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-03-25T14:07+0300
2024-03-25T14:07+0300
2025-03-26T11:14+0300
африка общий
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/images/sharing/article/amh/504.jpg?1742976895
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ትላንት ባወጣው መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የክልል ልዩ ሀይልን መልሶ የማደራጀት ውሳኔ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ በአማራ ክልል ውጥረት መንገሱን አስታውሶ ሐምሌ 28 በክልሉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ከታወጀ ሶስት ቀን በኋላ የ “አልፋ ሚዲያ” መስራች በቃሉ አላምረው ለእስር መዳረጉን ገልጧል፡፡ በቃሉ ፍርድ ቤት አለመቅረቡን እና በምን ምክንያት እንደታሰረ እንዳልተነገረው ቡድኑ አስታውቀቋል፡፡በተጨማሪም አማራ ሚዲያ ማዕከል የተሰኘ የዩቱዩብ ቻናል ዳይሬክተር የሆነው አባይ ዘውድ ከሐምሌ 3 ቀን ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል ያለው የቡድኑ መግለጫ በተመሳሳይ መልኩ አፍሪ ነጋሪ የተሰኘ ሚዲያ መስራች የሆነው ይድነቃቸው ከበደ በዚሁ ሳምንት ሀሙስ ነሃሴ 11 ቀን ከመኖሪያ ቤቱ ተይዞ ለእስር መዳረጉን ገልጧል፡፡ ይድነቃቸው በቁጥጥር ስር የዋለው በቅርቡ በአማራ ክልል የተከሰተውን ሁነት በመዘገቡ መሆኑን እና በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ 4ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ገልጧል፡፡“እነዚህ እስራት የመንግስትን ተቺዎች ዝም ለማሰኘት ባለስልጣናቱ የጀመሩት ሰፊ እንቅስቃሴ አካል ሲሆን ከዚህ አመት መጀመሪያ ጀምሮ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔርተኝነት አቀንቃኞችን በእስር ላይ ይገኛሉ” ሲል ገልጧል።“ከሚያዚያ ወር ጀምሮ በክልሉ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚፈፀመው የጋዜጠኞች እስር የኢትዮጵያ መንግስት ስላለው ውጥረት ሚዲያዎች ገለልተኛ ሽፋን እንዳይሰጡ የማድረግ ስትራቴጂው ነው፤ ጋዜጠኞች የዘፈቀደ እስራት ስጋት ሳይኖርባቸው ትችት መሰንዘር ወይም የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ መስጠት አይችሉም። የድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ቡድን ጋዜጠኞቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አጥብቆ ይጠይቃል” ሲሉ የድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ቡድን ከሰሃራ በታች ዳይሬክተር ሳዲቦ ማሮንግ ገልፀዋል፡፡ አስ
африка общий
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2024
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
африка общий
በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ዙሪያ ዘገባ በመስራታቸው የታሰሩ ጋዜጠኞችን መንግስት
14:07 25.03.2024 (የተሻሻለ: 11:14 26.03.2025) ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ትላንት ባወጣው
መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የክልል ልዩ ሀይልን መልሶ የማደራጀት ውሳኔ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ በአማራ ክልል ውጥረት መንገሱን አስታውሶ ሐምሌ 28 በክልሉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ከታወጀ ሶስት ቀን በኋላ የ “አልፋ ሚዲያ” መስራች በቃሉ አላምረው ለእስር መዳረጉን ገልጧል፡፡ በቃሉ ፍርድ ቤት አለመቅረቡን እና በምን ምክንያት እንደታሰረ እንዳልተነገረው ቡድኑ አስታውቀቋል፡፡በተጨማሪም አማራ ሚዲያ ማዕከል የተሰኘ የዩቱዩብ ቻናል ዳይሬክተር የሆነው አባይ ዘውድ ከሐምሌ 3 ቀን ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል ያለው የቡድኑ መግለጫ በተመሳሳይ መልኩ አፍሪ ነጋሪ የተሰኘ ሚዲያ መስራች የሆነው ይድነቃቸው ከበደ በዚሁ ሳምንት ሀሙስ ነሃሴ 11 ቀን ከመኖሪያ ቤቱ ተይዞ ለእስር መዳረጉን ገልጧል፡፡ ይድነቃቸው በቁጥጥር ስር የዋለው በቅርቡ በአማራ ክልል የተከሰተውን ሁነት በመዘገቡ መሆኑን እና በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ 4ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ገልጧል፡፡“እነዚህ እስራት የመንግስትን ተቺዎች ዝም ለማሰኘት ባለስልጣናቱ የጀመሩት ሰፊ እንቅስቃሴ አካል ሲሆን ከዚህ አመት መጀመሪያ ጀምሮ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔርተኝነት አቀንቃኞችን በእስር ላይ ይገኛሉ” ሲል ገልጧል።“ከሚያዚያ ወር ጀምሮ በክልሉ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚፈፀመው የጋዜጠኞች እስር የኢትዮጵያ መንግስት ስላለው ውጥረት ሚዲያዎች ገለልተኛ ሽፋን እንዳይሰጡ የማድረግ ስትራቴጂው ነው፤ ጋዜጠኞች የዘፈቀደ እስራት ስጋት ሳይኖርባቸው ትችት መሰንዘር ወይም የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ መስጠት አይችሉም። የድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ቡድን ጋዜጠኞቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አጥብቆ ይጠይቃል” ሲሉ የድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ቡድን ከሰሃራ በታች ዳይሬክተር ሳዲቦ ማሮንግ ገልፀዋል፡፡ አስ