https://amh.sputniknews.africa
የምግብ እርዳታ ላልታለመለት አላማ እየዋለ የሚገኘው በተቀናጀ፣ በተደራጀ መንገድ መሆኑ ተገለጸ፤
የምግብ እርዳታ ላልታለመለት አላማ እየዋለ የሚገኘው በተቀናጀ፣ በተደራጀ መንገድ መሆኑ ተገለጸ፤
Sputnik አፍሪካ
የአለም የምግብ ፕሮግራም እና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ በትግራይ ክልል ተፈጸመ በተባለው ለተረጂዎች የቀረበ የምግብ እርዳታ ላልታለመለት አላማ ውሏል በሚል ማቋረጣቸው ይታወቃል። 25.03.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-03-25T18:36+0300
2024-03-25T18:36+0300
2025-04-14T11:49+0300
африка общий
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/images/sharing/article/amh/1575.jpg?1744620597
በኢትዮጵያ የሚገኙ ለጋሽ ድርጅቶች በጋራ ያዘጋጁት እና ለአዲስ ስታንዳርድ የደረሰው የውስጥ ማስታወሻ እንደሚያሳየው ከሆነ ድርጊቱ የተፈጸመው በትግራይ ብቻ አይደለም፤ ተግባሩ የፌደራል እና የክልል ተቋማትን ያሳተፈ በሰባት ክልሎች የተፈጸመ ነው። የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ ላለፉት ሁለት ወራት ባካሄደው ሰፊ ክትትል እና ምርመራ በኢትዮጵያ በለጋሽ ድርጅቶች የሚቀርብ የምግብ እርዳታ ላልታለመለት አላማ እየዋለ የሚገኘው በሀገር አቀፍ ደረጃ መሆኑን ማረጋገጡን የውስጥ ማስታወሻው አመላክቷል። ድርጊቱ በተቀናጀ መልኩ በተወሳሰበ የወንጀል መንገድ እንደሚፈጸም የጠቆመው ሰነዱ የምግብ እርዳታው ለተጎጂዎች እንዳይደርስ ድርጊቱ እንቅፋት መሆኑን አስታውቋል።ተግባሩ የተፈጸመው የፌደራል እና የክልል ተቋማትን ባሳተፈ መልኩ መሁኑን የጠቆመው የምርመራ ውጤቱ ማስታወሻ የሀገሪቱ የመከላከያ ተቋም ክፍሎች ከሰብአዊ ረድኤቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን አመላክቷል። በዱቄት እና እህል ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦች ተግባሩን በማመቻቸት ረገድ ሚና እንደነበራቸውም አስታውቋል።የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ ባደረገው ክትትል ሌሎች ለጋሽ ሀገራት እና ድርጅቶች በሀገሪቱ ለሚገኙ ተጎጂዎች እንዲደርስ ያቀረቡት እርዳታ ላልታለመለት አላማ መዋሉን ማረጋገጡን ጠቁሟል። ከፈረንሳይ፣ ጃፓን እና ዩክሬን የተገኙ በአለም የምግብ ፕሮግራም አማካኝነት የቀረቡ እርዳታዎች ላልታለመለት አላማ መዋሉን ምርመራው ማረጋገጡን የውስጥ ማስታወሻው ላይ ተጠቅሷል።እንደ ውስጥ ማስታወሻው ከሆነ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ በመላ ሀገሪቱ የሚያካሂደውን የምግብ እርዳታ አቅርቦት ሊያቋርጥ የሚችልበት እድል ሰፊ መሆኑን ያሳያል። የአሜሪካን መንግስት በ2022 ብቻ የአንድ ነጥብ ስምንት ቢሊየን ዶላር የህይወት አድን እርዳታ መለገሱ ይታወሳል።ምንም እንኳ የተራድኦ ድርጅቱ የረድኤት ማቋረጥ ውሳኔ ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎች ላይ ተጽእኖ ባይኖረውም ከዚህ በኋላ በአሜሪካ መንግስት እገዛ የሚካሄዱ ቀጣይ እርዳታዎች ከመከፋፈላቸው በፊት የሀገሪቱ የሰብአዊ ረድኤት ተደራሽነት አሰራር አስቸኳይ እና አስፈላጊ የመዋቅር ማሻሻያ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ተገልጿል።
африка общий
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2024
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
африка общий
በኢትዮጵያ የሚገኙ ለጋሽ ድርጅቶች በጋራ ያዘጋጁት እና ለአዲስ ስታንዳርድ የደረሰው የውስጥ ማስታወሻ እንደሚያሳየው ከሆነ ድርጊቱ የተፈጸመው በትግራይ ብቻ አይደለም፤ ተግባሩ የፌደራል እና የክልል ተቋማትን ያሳተፈ በሰባት ክልሎች የተፈጸመ ነው። የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ ላለፉት ሁለት ወራት ባካሄደው ሰፊ ክትትል እና ምርመራ በኢትዮጵያ በለጋሽ ድርጅቶች የሚቀርብ የምግብ እርዳታ ላልታለመለት አላማ እየዋለ የሚገኘው በሀገር አቀፍ ደረጃ መሆኑን ማረጋገጡን የውስጥ ማስታወሻው አመላክቷል። ድርጊቱ በተቀናጀ መልኩ በተወሳሰበ የወንጀል መንገድ እንደሚፈጸም የጠቆመው ሰነዱ የምግብ እርዳታው ለተጎጂዎች እንዳይደርስ ድርጊቱ እንቅፋት መሆኑን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ እና መልሶ ማቋቋም ለጋሽ ድርጅቶች ቡድን በሰባት ክልሎች በሚገኙ 63 የዱቄት ፋብሪካዎች ላይ ያደረገው ክትትል እና ምርመራ የቀረቡ የምግብ እርዳታ እህሎች ላልታለመለት አላማ መዋሉን ማረጋገጡን በውስጥ ማስታወሻው ተጠቅሷል።
ተግባሩ የተፈጸመው የፌደራል እና የክልል ተቋማትን ባሳተፈ መልኩ መሁኑን የጠቆመው የምርመራ ውጤቱ ማስታወሻ የሀገሪቱ የመከላከያ ተቋም ክፍሎች ከሰብአዊ ረድኤቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን አመላክቷል። በዱቄት እና እህል ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦች ተግባሩን በማመቻቸት ረገድ ሚና እንደነበራቸውም አስታውቋል።
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ ባደረገው ክትትል ሌሎች ለጋሽ ሀገራት እና ድርጅቶች በሀገሪቱ ለሚገኙ ተጎጂዎች እንዲደርስ ያቀረቡት እርዳታ ላልታለመለት አላማ መዋሉን ማረጋገጡን ጠቁሟል። ከፈረንሳይ፣ ጃፓን እና ዩክሬን የተገኙ በአለም የምግብ ፕሮግራም አማካኝነት የቀረቡ እርዳታዎች ላልታለመለት አላማ መዋሉን ምርመራው ማረጋገጡን የውስጥ ማስታወሻው ላይ ተጠቅሷል።
እንደ ውስጥ ማስታወሻው ከሆነ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ በመላ ሀገሪቱ የሚያካሂደውን የምግብ እርዳታ አቅርቦት ሊያቋርጥ የሚችልበት እድል ሰፊ መሆኑን ያሳያል። የአሜሪካን መንግስት በ2022 ብቻ የአንድ ነጥብ ስምንት ቢሊየን ዶላር የህይወት አድን እርዳታ መለገሱ ይታወሳል።
ምንም እንኳ የተራድኦ ድርጅቱ የረድኤት ማቋረጥ ውሳኔ ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎች ላይ ተጽእኖ ባይኖረውም ከዚህ በኋላ በአሜሪካ መንግስት እገዛ የሚካሄዱ ቀጣይ እርዳታዎች ከመከፋፈላቸው በፊት የሀገሪቱ የሰብአዊ ረድኤት ተደራሽነት አሰራር አስቸኳይ እና አስፈላጊ የመዋቅር ማሻሻያ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ተገልጿል።