https://amh.sputniknews.africa
በፍኖተሰላም በአየር ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 30 ደርሷል፤ ዶክተሮች የገጠማቸው
በፍኖተሰላም በአየር ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 30 ደርሷል፤ ዶክተሮች የገጠማቸው
Sputnik አፍሪካ
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተሰላም ከተማ የአየር ድብደባ ሊሆን ይችላል በተባለ ጥቃት ቢያንስ 30 ሰዎች ሲሞቱ ከ 55 ባለይ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሶባቸው በከተማው በሚገኝ ፍኖተሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና ላይ መሆናቸውን የሆስፒታሉ ስራ... 25.03.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-03-25T17:51+0300
2024-03-25T17:51+0300
2025-04-14T11:53+0300
африка общий
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/images/sharing/article/amh/1050.jpg?1744620790
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ የሆኑት ማናዬ ጤናው ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ጥቃቱ የተፈፀመው እሁድ ነሃሴ 7 ቀን 2015 ዳሞት በሚባል ሆቴል አጠገብ ነው፡፡ “ጠዋት ላይ ከባድ የፍንዳታ ድምፅ ተሰማን ከዚያ ወዲያውኑ በርካታ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሆስፒታሉ መምጣት ጀመሩ” ሲሉ የገለፁት ኃላፊው ሁሉ ተጎጂዎቹ ወንዶች መሆናቸውን ጠቅሰው እድሜያቸው በ20ዎቹ ውስጥ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የከተማው ነዋሪ ጥቃቱ ጠዋት ወደ 4 ሰዓት መፈፀሙን ገልፆ የጥቃቱ ሰላባ የሆኑት ሰዎች በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት በከባድ ተሸከርካሪ ወደ ማንኩሳ ለመጓዝ በዝግጅት ላይ ነበሩ ሲል ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድቷል፡፡ ነዋሪው በተሽከርካሪው ውስጥም ሆነ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በጥቃቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጿል።ነዋሪ አክሎም “ ጥቃቱ የደረሰው በሰው አልባ አውሮፕላን ሳይሆን እንዳልቀሰ ጠቅሶ ምናልባትም ቦምብ ወይም ሌላ ከባድ መሳሪያ ሊሆን እንደሚችልም ተናግሯል።የፍኖተሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ማናዬ ጤናው ለሁለት ሳምንታት ያህል በዘለቀው የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጥ ሳቢያ የህክም አቅርቦቶችና የኦክስጂን እጥረት መከሰቱን ገልፀዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ሰዎች እየሞቱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ስራ አስኪያጁ ተጨማሪ ሞት እንዳይከሰት የትራንስፖርት አገልግሎትን ወደነበረበት በመመለስ እና አስፈላጊ የሆኑ የህክምና አቅርቦቶች ለማድረስ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ለሚመለከታቸው አካላት ተማፅነዋል።
африка общий
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2024
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
африка общий
በፍኖተሰላም በአየር ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 30 ደርሷል፤ ዶክተሮች የገጠማቸው
17:51 25.03.2024 (የተሻሻለ: 11:53 14.04.2025) የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ የሆኑት ማናዬ ጤናው ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ጥቃቱ የተፈፀመው እሁድ ነሃሴ 7 ቀን 2015 ዳሞት በሚባል ሆቴል አጠገብ ነው፡፡ “ጠዋት ላይ ከባድ የፍንዳታ ድምፅ ተሰማን ከዚያ ወዲያውኑ በርካታ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሆስፒታሉ መምጣት ጀመሩ” ሲሉ የገለፁት ኃላፊው ሁሉ ተጎጂዎቹ ወንዶች መሆናቸውን ጠቅሰው እድሜያቸው በ20ዎቹ ውስጥ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የከተማው ነዋሪ ጥቃቱ ጠዋት ወደ 4 ሰዓት መፈፀሙን ገልፆ የጥቃቱ ሰላባ የሆኑት ሰዎች በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት በከባድ ተሸከርካሪ ወደ ማንኩሳ ለመጓዝ በዝግጅት ላይ ነበሩ ሲል ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድቷል፡፡ ነዋሪው በተሽከርካሪው ውስጥም ሆነ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በጥቃቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጿል።
ነዋሪ አክሎም “ ጥቃቱ የደረሰው በሰው አልባ አውሮፕላን ሳይሆን እንዳልቀሰ ጠቅሶ ምናልባትም ቦምብ ወይም ሌላ ከባድ መሳሪያ ሊሆን እንደሚችልም ተናግሯል።
የፍኖተሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ማናዬ ጤናው ለሁለት ሳምንታት ያህል በዘለቀው የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጥ ሳቢያ የህክም አቅርቦቶችና የኦክስጂን እጥረት መከሰቱን ገልፀዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ሰዎች እየሞቱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ስራ አስኪያጁ ተጨማሪ ሞት እንዳይከሰት የትራንስፖርት አገልግሎትን ወደነበረበት በመመለስ እና አስፈላጊ የሆኑ የህክምና አቅርቦቶች ለማድረስ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ለሚመለከታቸው አካላት ተማፅነዋል።