የሶማሊያ ተገንጣይ ግዛት ሶማሌላንድ የቱርክ ባህር ኃይል በውሃዋ ላይ መሰማራቱን እንደማትቀበል ገለፀች "ማንኛውም ውጫዊ የአንድ ጎን ድርጊቶች፤ ለምሳሌ የቱርክ ባህር ኃይል በሶማሌላንድ የባህር ክልል ውስጥ እንዲሰማራ እንዳሰበ የሚገልፁ ሪፖርቶች የዓለም አቀፍ ህግን እና የሶማሌላንድን ሉዓላዊ መብቶች የሚጥስ ነው" ሲል የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ አክሎም "እንዲህ አይነት ድርጊቶች ክልላዊ መረጋጋትን የሚሸረሽር እና በአጎራባች ክልሎች መካከል ያለውን በሰላም አብሮ የመኖር መንፈስ የሚቃረን" ነው ብሏል። የሶማሌላንድ ተቃውሞ በአካባቢው መረጋጋት ለማስፈን ያስችላል የተባለ የመከላከያ ስምምነት በሶማሊያ እና ቱርክ መካከል ከተደረገ በኋላ የመጣ ነው። ይህም ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን የባህር በር ስምምነት የተከተለ ሲሆን በስምምነቱ መሰረት አዲስ አበባ በቀይ ባህር ወደብ ስታገኝ ሶማሌላንድ ከምእራብ ጎረቤትዋ ለነፃነቷ እውቅና እንድታገኝ የሚያስችላት ነው። የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን በአፍሪካ ቀንድ ሶስት የባህር ዳርቻዎች ላይ የዘይት እና ጋዝ ፍለጋ የሚያካሂድ የምርምር መርከብን ለማጀብ የቱርክ ባህር ኃይልን በአከባቢው ለማሰማራት የፓርላማ ይሁንታን ጠይቀዋል። መርከቡን በመስከረም መጨረሻ ወደ አካባቢው ለማንቀሳቀስ እቅድ ተይዟል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa/20240727/6301.html
የሶማሊያ ተገንጣይ ግዛት ሶማሌላንድ የቱርክ ባህር ኃይል በውሃዋ ላይ መሰማራቱን እንደማትቀበል ገለፀች
የሶማሊያ ተገንጣይ ግዛት ሶማሌላንድ የቱርክ ባህር ኃይል በውሃዋ ላይ መሰማራቱን እንደማትቀበል ገለፀች
Sputnik አፍሪካ
የሶማሊያ ተገንጣይ ግዛት ሶማሌላንድ የቱርክ ባህር ኃይል በውሃዋ ላይ መሰማራቱን እንደማትቀበል ገለፀች "ማንኛውም ውጫዊ የአንድ ጎን ድርጊቶች፤ ለምሳሌ የቱርክ ባህር ኃይል በሶማሌላንድ የባህር ክልል ውስጥ እንዲሰማራ እንዳሰበ የሚገልፁ ሪፖርቶች የዓለም... 27.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-27T12:40+0300
2024-07-27T12:40+0300
2024-07-27T13:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የሶማሊያ ተገንጣይ ግዛት ሶማሌላንድ የቱርክ ባህር ኃይል በውሃዋ ላይ መሰማራቱን እንደማትቀበል ገለፀች
12:40 27.07.2024 (የተሻሻለ: 13:20 27.07.2024)
ሰብስክራይብ