የሐምሌ 8 ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የሐምሌ 8 ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች 🟠 የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የዩክሬን ግጭትን ለማስቆም ያላቸውን የሰላም እቅድ እ.አ.አ ሐምሌ 18 በእንግሊዝ በሚካሄደው የአውሮፓ የፖለቲካ ማህበረሰብ ጉባኤ ላይ ሊያቀርቡ እንደሚችሉ የአውሮፓ ህብረት ምንጭ ገልጿል። 🟠 ኦቶ የተባለ ጡረተኛ ጀርመናዊ አልሞ ተኳሽ በዩክሬን በኩል ተሰልፎ ፤ በቻሶቭ ያር ዲፒአር አቅራቢያ በሚካሄደው ውጊያ ላይ እየተሳተፈ መሆኑን የዴር ስፒገል  አንድ ዘገባ አትቷል። በቴሌቪዥኑ ዘገባ መሠረት አልሞ ተኳሹ 49 ዓመቱ ሲሆን ከባቫሪያ ግዛት እ.አ.አ በ 2022 ወደ ዩክሬይን እንደመጣ ተመላክቷል። 🟠 27 ሰዎች በዩክሬን ወደ ሞልዶቫ ለመሻገር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተገልጿል። ድንበሩን ለመሻገር ከ 4 ሺ እስከ 7 ሺህ ዶላር መክፈል እንደሚጠበቅባቸው የዩክሬን የድንበር አገልግሎት አስታውቋል። 🟠 የፍሎሪዳ ፍርድ ቤት የዩናይትድ ስቴትስ እጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሚስጥራዊ ሰነዶችን በህገ ወጥ መንገድ በመያዝ የልዩ ካውንስል ህጎችን ጥሰዋል በሚል የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አድርጓል። እሁድ እለት በነበረው የድጋፍ ሰልፍ  ላይ ከተተኮሰባቸው ጥይት ከተረፉ በኋላ፤ ወዲያውኑ እንደተናገሩት ባይደን የፍትህ ዲፓርትመንት በእርሳቸው ላይ የተከፈቱት ሁለት ክሶችን እንዲያቋርጥ ሊጠይቅ እንደሚችል ተናግሯል። 🟠 አሜሪካዊው ቢሊየነር ኢሎን መስክ በዶናልድ ትራምፕ የድጋፍ ሰልፍ ወቅት ለእጩ ፕሬዝደንቱ ተገቢውን የደህንነት ጥበቃ ማድረግ አልቻለም በማለት የአሜሪካ ደህንነት አገልግሎትን ከሰሰ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0