ሶማሊያ አፍሪ ኤግዚም ባንክን ተቀላቀለች

ሰብስክራይብ
ሶማሊያ አፍሪ ኤግዚም ባንክን ተቀላቀለች በዚህም የኢንቨስትመንት ዕድሎች፣ የተመቻቸ ንግድ እና የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ማግኘት እንድትችልና ኢኮኖሚዋን መልሳ እንድትገነባ ይረዳታል ሲል ባንኩ ገልጿል። የሶማሊያ ሚኒስትር ዴኤታ ሂርሲ ጃማ ጋኒ ለሀገሪቱ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው ያሉት ሲሆን ሶማሊያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ሥር በክልላዊና አህጉራዊ ንግድ ውስጥ ለሚኖራት ሚና ቁርጠኝነቷን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል። የአፍሪ ኤግዚም ባንክ ሰብሳቢ ቤኔዲክት ኦራማ የሶማሊያ አባልነት ለመንግሥት እና የግል ዘርፎች አዲስ የገንዘብ ድጋፍ አማራጮችን የሚፈጠር ነው ብለዋል። የሶማሊያ የንግድና የፋይናንስ ዘርፎች ከባንኩ የልማት ተነሳሽነቶች ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋገጡ ውይይቶች ከወዲሁ መካሄድ እንደጀመሩም ተጠቁሟል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0