በተባባሰው የሱዳን ጦርነት በትንሹ 15 ሺህ አባወራዎች ከሰሜን ዳርፉሯ ከተማ አል ማልሃ ተሰደዋል ሲል ተመድ ገለፀ

ሰብስክራይብ
በተባባሰው የሱዳን ጦርነት በትንሹ 15 ሺህ አባወራዎች ከሰሜን ዳርፉሯ ከተማ አል ማልሃ ተሰደዋል ሲል ተመድ ገለፀ የሱዳን ፈጣኖ ደራሽ ኃይል አል ማልሃን እንደተቆጣጠረ ያስታወቀው ሐሙስ ዕለት ነበር። በከተማው በተካሄደው ጦርነት ቢያንስ 45 ንፁሃኖች እንደተገደሉ ተሟጋቾች ተናግረዋል። "በመጋቢት 11 እና 12 መካከል በሱዳን የጦር ኃይሎች፣ በጁባ የሰላም ስምምነት የጋራ ኃይሎች እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል በተካሄደው ውጊያ ምክንያት መፈናቀል ተከስቷል" ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) አስታውቋል።ተመድ ሁኔታው አሁንም የተካረረ እና ተጠባቂ እንዳልሆነ ገልፆ፤ አብዛኛው ሕዝብ በአል ማልሃ አቅራቢያ በሚገኙ ቦታዎች እንደተሰደደ አመልክቷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0