የአልጀርያ ድርጅቶች በኢትዮጵያ የኃይል ልማት ዘርፍ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

ሰብስክራይብ
የአልጀርያ ድርጅቶች በኢትዮጵያ የኃይል ልማት ዘርፍ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበጥሪው የቀረበው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ ከአልጀሪያ የኢነርጂ፣ ማዕድንና ታዳሽ ኢነርጂ ሚኒስትር መሃመድ አርካብ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡በውውይቱ ኢነርጂ ላይ የሚሠሩ የአልጀሪያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኃይል ልማት ዘርፍ ላይ መሳተፍ የሚችሉበት መልካም አጋጣሚ እንዳለ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ በሚወጡ ዓለም አቀፍ የኢነርጂ ጨረታዎች ላይ የአልጀርያ ድርጅቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የአልጀሪያ የኢነርጂ ማዕድንና ታዳሽ ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር መሃመድ አርካብ በበኩላቸው ሶኔለጋዝ እና ሶናትራክ የመሳሰሉ የአልጀሪያ የኃይል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መሠማራት እንደሚፈልጉ መግለፃቸውን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0