ኢትዮጵያ በባህል ዲፕሎማሲ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተች ነው ሲሉ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በባህል ዲፕሎማሲ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተች ነው ሲሉ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ተናገሩ በአዲስ አበባ የተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል ፓን አፍሪካኒዝምን አጉልቶ ለማሳየት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ሲሉም የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማሃዲ ከሁለተኛ የምስራቅ አፍሪካ የባህል እና ሥነ-ጥበብ ፌስቲቫል ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም የኢትዮጵያ የባህል ዲፕሎማሲ ከአፍሪካም አልፎ የሚሻገር ነው ብለዋል።"ለምሳሌ በዚህ ዝግጅት ላይ ወደ ስምንት ሀገራት ናቸው የመጡት። ለነዚህ ስምንት ሀገራት ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ እና ፓን አፍሪካኒዝም አጉልቶ ለማሳየት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ኢትዮጵያ በባህል ዲፕሎማሲ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተች ያለች ሀገር ናት። ከአፍሪካም አልፋ ለዓለም የተለያዩ የኪነጥበብ ሥራዎች እየቀረቡ ትልቅ አድናቆት ያገኙ የኪነጥበብ ሥራዎች አሉን። እናም ይሄ የኢትዮጵያን ማንነት በጣም ከፍ ያደርጋል። በሌላ መንገድም ኢትዮጵያ በተለያዩ ሀገራት ሰላምን ከማስፈን አኳያ ትልቅ አስተዋጽኦ ያላት ሀገር እንደመሆኗ፤ ይሄ ፓን አፍሪካኒዝምን ከፍ ለማድረግ በጣም ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።" "ጥበብና ባህል ለቀጠናዊ ትስስር " በሚል መሪ ቃል በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ሲካሄድ የቆየው ሁለተኛው የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል በትናንትናው እለት ተጠናቋል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0