በኢትዮጵያ የከብቶች ሳንባ በሽታን ለመዋጋት የምርመራ እና ልየታ ዘዴ የተሻለ አማራጭ ሆኖ እንደተገኘ አንድ ጥናት ጠቆመበጣም ተላላፊ እና አደገኛ የሆነው የባክቴሪያ በሽታ ከብቶችን እና ሌሎች የቤት እንስሳትን ያጠቃል። በኢትዮጵያ ብቻ በግምት 3.8 ሚሊዮን ከብቶችን እንደሚያጠቃ ጥናቶች የሚጠቁሙ ሲሆን በዚህም ሀገሪቱ 2.4 በመቶ ከእንስሳት ወደ ሰው ለሚተላለፍ የሳንባ በሽታ ተጋላጭ ናት። በሽታውን ለመቆጣጠር የተለመደው አሠራር መርምሮ በበሽታው የተያዙትን ማረድ ቢሆንም ኢትዮጵያ እና ሌሎችም ሀገራት በኢኮኖሚ፣ መሠረተ ልማት፣ ሐይማኖታዊ እና ባሕላዊ ምክንያቶች ይህን ዘዴ አይጠቀሙም። የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል ከብቶችን መርምሮ ባክቴርያው የተገኘባቸውን በመለየት ቀሪዎቹን የመከላከል ዘዴ ውጤታማ እንደሆነ በሰበታ የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት የእንስሳት ሐኪምና ተመራማሪ ዶ/ር ማቲዮስ ላቀው ገልፀዋል። መርምሮ በበሽታው የተያዙትን የማረድ ዘዴ ብዙ መሠረተ ልማት ባይጠይቅም መርምሮ ከመለየት በሁለት እጥፍ ወድ እንደሆነ ጥናቱ ማረጋገጡን ባለሙያው ጨምረው ገልፀዋል። ሆኖም እርሻዎች በቲቢ የተያዙትን ካልተያዙት የሚለይ በቂ የለይቶ ማቆያ ቦታ ሊኖራቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።የዓለም ቲቢ ቀን በየዓመቱ መጋቢት 15 ቀን የሚከበር ሲሆን ቀኑ ቲቢን መከላከልና መቆጣጠር አስፈላጊ እንደሆነ በማጉላት ታስቦ ይውላል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
https://amh.sputniknews.africa
በኢትዮጵያ የከብቶች ሳንባ በሽታን ለመዋጋት የምርመራ እና ልየታ ዘዴ የተሻለ አማራጭ ሆኖ እንደተገኘ አንድ ጥናት ጠቆመ
በኢትዮጵያ የከብቶች ሳንባ በሽታን ለመዋጋት የምርመራ እና ልየታ ዘዴ የተሻለ አማራጭ ሆኖ እንደተገኘ አንድ ጥናት ጠቆመ
Sputnik አፍሪካ
በኢትዮጵያ የከብቶች ሳንባ በሽታን ለመዋጋት የምርመራ እና ልየታ ዘዴ የተሻለ አማራጭ ሆኖ እንደተገኘ አንድ ጥናት ጠቆመበጣም ተላላፊ እና አደገኛ የሆነው የባክቴሪያ በሽታ ከብቶችን እና ሌሎች የቤት እንስሳትን ያጠቃል። በኢትዮጵያ ብቻ በግምት 3.8... 24.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-24T20:23+0300
2025-03-24T20:23+0300
2025-03-24T20:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በኢትዮጵያ የከብቶች ሳንባ በሽታን ለመዋጋት የምርመራ እና ልየታ ዘዴ የተሻለ አማራጭ ሆኖ እንደተገኘ አንድ ጥናት ጠቆመ
20:23 24.03.2025 (የተሻሻለ: 20:44 24.03.2025)
ሰብስክራይብ