አንጎላ ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭት አሸማጋይነቷ እራሷን አገለለች

ሰብስክራይብ
አንጎላ ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭት አሸማጋይነቷ እራሷን አገለለችአዲሱን የአፍሪካ ሕብረት የሊቀመንበርነት ኃላፊነት የጠቀሰው የአንጎላ መንግሥት፤ ትኩረቱን ሰፋ ወዳሉ ቀዳሚ አህጉራዊ ጉዳዮች እንደሚያዞር አስታውቋል። ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን፣ ከደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳድክ) እና ከምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (ኢኤሲ) ጋር በመሆን አዲስ አሸማጋይ እንደሚፈልግም ገልጿል። ውሳኔው የኮንጎ መንግሥት እና ኤም23 ሉዋንዳ ላይ ሊያደርጉት የነበረው ቀጥተኛ ድርድር ከከሸፈ በኋላ የመጣ ነው። ለመጋቢት 9 ተይዞ የነበረው ውይይት ኤም23 ለመሳተፍ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ሳይሳካ ቀርቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩዋንዳ መንግሥት የኤም23 አማፂ ቡድንን ከዋሊካሌ መውጣት እና የኮንጎ መንግሥት ግጭቱን የማቆም ውሳኔ በበጎው እንደሚቀበል እሁድ ዕለት ገልጿል። ሩዋንዳ በኢኤሲ-ሳድክ ጉባኤ ማዕቀፍ የፖለቲካ እና የደህንነት መፍትሄዎች አስፈላጊነትን በማጉላት ለሰላም ጥረቶች ቁርጠኝነቷን አረጋግጣለች። ሆኖም ኤም23 ለሰላም ጥረቶች በሚል ኃይሉን ከዋሊካሌ እንደሚያስወጣ ካሳወቀ በኋላ የኮንጎ ወታደሮች የድሮን ጥቃቶችን በመቀጠላቸው ሂደቱን አደናቅፈዋል ሲል ቡድኑ ከሷል። ኤም23ን የሚያካተተው የኮንጎ ወንዝ ጥምረት ጥቃቱ የተኩስ አቁም እና ቀጣይ የሰላም ተነሳሽነቶችን እንደሚያሰናክል አስጠንቅቋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0