ከአሜሪካ የተባረሩት የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር የጀግና አቀባበል ተደረገላቸው

ሰብስክራይብ
ከአሜሪካ የተባረሩት የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር የጀግና አቀባበል ተደረገላቸው"ምርጫችን ባይሆንም ወደ ቤት በመመለሳችን ግን አንጸጸትም።...እንደዚህ ዓይነት አቀባበል ሲደረግልን በደቡብ አፍሪካ ነጮች ላይ የዘር ማጥፋት አለ የሚሉ ውሸቶችን ውድቅ እንዳደረግን በወደድን ነበር፤ ነገር ግን በአሜሪካ ይህን ለማሳካት አልቻልንም" ሲሉ ኬፕ ታውን ሲደርሱ በደጋፊዎቻቸው ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው አምባሳደር ኢብራሂም ራሱል ተናግረዋል። "በመጋቢት ወር አጋማሽ ከአሜሪካ እንዲወጡ የተነገራቸው ዲፕሎማቱ፤ ደቡብ አፍሪካ ከአሜሪካ ጋር ከ50 ዓመት በላይ ያስቆጠረ ግንኙነቷን 'ማስተካከልና እንደገና መገንባት' እንዳለባት ተናግረዋል። ግንኙነቱ መጠገን ያለበት ግን 'የደቡብ አፍሪካን እሴቶች አሳልፎ በመስጠት' እንዳልሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል።"ፍልስጤማውያንን መስዋዕት ማድረግ የለብንም። ብሪክስን አንተውም። ከቻይና ጋር ያለንን ግንኙነት አናቆምም። ከአሜሪካ ጋር ያለንን አጋርነትም አንተውም። መታገል ይኖርብናል፤ ክብራችንን ግን መጠበቅ አለብን" ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0