ጃፓን በሀገሪቱ የተከሰተውን የሰደድ እሳት ለማጥፋት ሠራዊቷን አሠማራች

ሰብስክራይብ
ጃፓን በሀገሪቱ የተከሰተውን የሰደድ እሳት ለማጥፋት ሠራዊቷን አሠማራችየጃፓን የምድር ኃይሎች በምዕራባዊ ግዛቶች በኦካያማ እና ኢሂሜ የእሳት አደጋ መከላከል ሥራዎችን እንደተቀላቀሉ የጃፓን ዋና የካቢኔ ፀሐፊ ዮሺማሳ ሃያሺ ተናግረዋል። ሰደድ እሳቱ እሁድ ዕለት ከተነሳ በኋላ በግዛቱ አስተዳዳሪዎች ጥያቄ መሠረት እርዳታ እንደተላከ ሃያሺ አክለዋል። ወደ 2 ሺህ 700 የሚጠጉ ነዋሪዎች አካባቢውን እንዲለቁ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ባለስልጣኑ ገልፀዋል። የእሳት ቃጠሎው በኢሂሜ 128 ሄክታር በኦካያማ ደግሞ በ250 ሄክታር ላይ ተስፋፍቷል ብለዋል። በጃፓን የመጨረሻው ትልቁ የእሳት ቃጠሎ በሰሜን ምስራቅ ኢዋቴ ግዛት በምትገኘው ኦፉናቶ ከተማ ለ12 ቀናት የዘለቀ ነበር፡፡ ወደ 3 ሺህ ሄክታር ወይም 9 በመቶ የሚሆነውን የከተማዋን አጠቃላይ ስፍራ ያወደመ ሲሆን ባለስልጣናት 4 ሺህ 500 ሰዎች አካባቢውን እንዲለቁ ትዕዛዝ እንደሰጡ ዘገባዎች አመልክተዋል። ቢያንስ አንድ ሰው እንደሞተ እና ከ200 በላይ ህንጻዎች እንደወደሙም ተዘግቧል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0