ሁለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት የጦር መሳሪያ ማስተኮሻ ሶፍትዌር ማበልፀጋቸው ተነገረ

ሰብስክራይብ
ሁለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት የጦር መሳሪያ ማስተኮሻ ሶፍትዌር ማበልፀጋቸው ተነገረ በአዋሽ አርባ ውጊያና ቴክኒክ ትምህርት ቤት ለሜካናይዝድ ስልጠና የገቡት ሁለቱ ወጣቶች፤ ከመደበኛ ስልጠናቸው ጎን ለጎን የጦር መሳሪያ ማስተኮሻ ሶፍትዌር አበልፅገው ለተቋማቸው አስረክበዋል።መሠረታዊ ወታደር ዘላለም ቤዛነህ እና መሠረታዊ ወታደር ዳንኤል ሙልቀን የፈጠሩት ሶፍትዌር ውጤታማነቱ እንደተረጋገጠ መከላከያ ሠራዊት በማህበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡በፈጠራቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የሙሉ አስር አለቅነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0