ዲልማ ሩሴፍ የብሪክስ የልማት ባንክ ኃላፊ ሆነው ዳግም ተመረጡ ሩሴፍ "ዳግም ተመርጫለሁ፣ ቦርዱ በአንድ ድምፅ አፅድቆታል" ማለታቸውን ጠቅሶ ኦ ግሎቦ ጋዜጣ ዘግቧል። በሩሲያ ካዛን በተካሄደው የብሪክስ ጉባዔ ሩሲያ የብራዚልን ሊቀመንበርነት እና የሩሴፍን የሥራ ዘመን ለማራዘም ሀሳብ አቅርባ ነበር።ዲልማ ሩሴፍ እ.አ.አ ከ2011 እስከ 2016 የብራዚል 36ኛ ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉ የኢኮኖሚክስ ምሑር እና ፖለቲከኛ ናቸው። የባንኩን የኃላፊንት ቦታ የያዙ የመጀመሪያዋ ሴትም ናቸው። በወጣትነታቸው የብራዚል ወታደራዊ አምባገነን ስርዓትን (1964-1985) በመቃወም በግራ ዘመም የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳትፈዋል። በ1970 በሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ በአገዛዙ ታስረው ነበር።በእስር ላይ እያሉ የተለያዩ አካላዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ማሰቃየቶች የደረሰባቸው ሲሆን ከተፈቱ በኋላ የትግል እንቅስቃሴያቸውን ቀጥለው በመጨረሻም የፖለቲካውን ዓለም ተቀላቅለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
https://amh.sputniknews.africa
ዲልማ ሩሴፍ የብሪክስ የልማት ባንክ ኃላፊ ሆነው ዳግም ተመረጡ
ዲልማ ሩሴፍ የብሪክስ የልማት ባንክ ኃላፊ ሆነው ዳግም ተመረጡ
Sputnik አፍሪካ
ዲልማ ሩሴፍ የብሪክስ የልማት ባንክ ኃላፊ ሆነው ዳግም ተመረጡ ሩሴፍ "ዳግም ተመርጫለሁ፣ ቦርዱ በአንድ ድምፅ አፅድቆታል" ማለታቸውን ጠቅሶ ኦ ግሎቦ ጋዜጣ ዘግቧል። በሩሲያ ካዛን በተካሄደው የብሪክስ ጉባዔ ሩሲያ የብራዚልን ሊቀመንበርነት እና የሩሴፍን... 24.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-24T13:41+0300
2025-03-24T13:41+0300
2025-03-24T14:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий