ኢትዮጵያ በ20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከአፍሪካ አንደኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በ20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከአፍሪካ አንደኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች በቻይና በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያ በ3000 ሜትር ሴቶች በፍሬወይኒ ሀይሉ እና በሴቶች 1500 ሜትር በጉዳፍ ፀጋይ የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች። በወንዶች 3000 ሜትር አትሌት በሪሁ አረጋዊ፣ በሴቶች 1500 ሜትር አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና በ800 ሜትር ሴቶች አትሌት ንግስት ጌታቸው ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አምጥተዋል። በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ እና ሶስት ብር ሜዳሊያ ከዓለም ሶስተኛ ከአፍሪካ ደግሞ በአንደኝነት ደረጃ መጨረሷን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0