ከኢትዮጵያ የወጪ ገቢ ጭነት ውስጥ ግማሹን በባቡር ለማጓጓዝ እንደታቀደ ተገለጸ

ሰብስክራይብ
ከኢትዮጵያ የወጪ ገቢ ጭነት ውስጥ ግማሹን በባቡር ለማጓጓዝ እንደታቀደ ተገለጸ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አ.ማ 50% የሚሆነውን የኢትዮጵያን የወጪ ገቢ ጭነት ለመሸፈን በየቀኑ 14 ባቡሮችን ለማሠማራት አቅዶ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጿል። በተጨማሪም የጭነት ባቡር ጉዞ ፍጥነትን በሰዓት ወደ 58 ኪሎ ሜትር ለማድረስ እንዲሁም በባቡር የሚሰጠውን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ዲጂታሊዝ ለማድረግ ማቀዱን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል። የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አ.ማ ጭነት የማጓጓዝ አቅሙን በየዓመቱ በ14.2 በመቶ እያሳደገ እንደመጣና ወደ ውጭ ከተላከው ቡና 98 በመቶ የሚሆነው በባቡር እንደተጓጓዘ ተገልጿል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0