‍ኢትዮጵያ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 3000 ሜትር ወርቅ አስመዘገበች

ሰብስክራይብ
‍ኢትዮጵያ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 3000 ሜትር ወርቅ አስመዘገበች በቻይና እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው ሻምፒዮና በሴቶች የ3000 ሜትር ፍጻሜ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ 8:37:21 በመግባት በአንደኝነት ጨርሳለች። "ይህን ውድድር ለማሸነፍ በርትቼ ተዘጋጅቼ ነበር። ውድድሩን በማሸነፌም በጣም ደስተኛ ነኝ። ወደ ናንጂንግ ከመምጣቴ በፊት ታምሜ ነበር። አሁን ጤንነቴ ተመልሷል፤ እዚህ የመጣሁት ለማሸነፍ ነው። ባለፈው ዓመት በ1500 ሜትር አሸናፊ ነበርኩ፤ አሁን ደግሞ 3000 ሜትርን አሸንፌያለሁ፤ በዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ" ስትል አትሌት ፍሬወይኒ ወድድሩን ካሸነፈች በኋላ ተናግራለች።በወንዶች 3000 ሜትር ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ ሁለተኛ ደረጃ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስገኝቷል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0