የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንድትስብ አድርጓታል ሲል ኮሚሽኑ አስታወቀ

ሰብስክራይብ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንድትስብ አድርጓታል ሲል ኮሚሽኑ አስታወቀ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ይህ ሊሆን የቻለው በአዲሱ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ሕግ ነው ብሏል። ኮሚሽኑ እነዚህ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የኢንዱስትሪ ፓርኮችን፣ የነፃ ንግድ ዞኖችን እንዲሁም የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ የአገልግሎት እና የእርሻ/የእንስሳት ፓርኮችን ጨምሮ የተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮችን እንደሚያካትቱ ገልጿል። ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ማበረታቻ ቁልፍ ሲሆን በኢትዮጵያ ኢንቨስት የሚያደርጉ ባለሀብቶች የግብር እፎይታ፣ ቀልጣፋ የንግድ ሂደቶች እና ጠንካራ የመሠረተ ልማት ማግኘት እንደሚችሉ አመልክቷል። ውጤታማ የልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ትግበራ ከፍተኛ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ የንግድ ተወዳዳሪነትን በማሳድግ እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማበረታታት፤ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶች ከኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ቦታ፣ እያደገ ካለው ገበያ እና ከምቹ የንግድ ሁኔታዎች እንዲጠቀሙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብሎ እንደሚያምን ኮሚሽኑ ገልጿል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0