ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎቿ ጋር የዕዳ አከፋፈል ስምምነት ላይ እንደደረሰች ገለፀች ስምምነቱ ያልተከፈለ 8.4 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ዕዳን እንደሚሸፍን ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከአባዳሪዎቿ ጋር በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ ሥር የዕዳ አከፋፈል ዋና የፋይናንስ መለኪያዎች ዙሪያ በመርህ ደረጃ እንደተስማማች የገንዘብ ሚኒስቴር በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ከውጭ አበዳሪዎቿ ጋር የዕዳ አከፋፈል ድርድር በማድረግ 3.5 ቢሊዮን ዶላር የዕዳ ክፍያ ለመቀነስ እና ብድር የመክፈል አቅሟን ለማሻሻል ቁርጠኛ እንደሆነች ገልጻለች። የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ "ስምምነቱ ከዓለም አቀፍ አጋሮቻችን ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስተካከል እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን ለማምጣት ለምናደርገው ጥረት ወሳኝ ምዕራፍ ነው" ብለዋል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎቿ ጋር የዕዳ አከፋፈል ስምምነት ላይ እንደደረሰች ገለፀች
ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎቿ ጋር የዕዳ አከፋፈል ስምምነት ላይ እንደደረሰች ገለፀች
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎቿ ጋር የዕዳ አከፋፈል ስምምነት ላይ እንደደረሰች ገለፀች ስምምነቱ ያልተከፈለ 8.4 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ዕዳን እንደሚሸፍን ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከአባዳሪዎቿ ጋር በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ ሥር የዕዳ አከፋፈል ዋና የፋይናንስ... 22.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-22T21:50+0300
2025-03-22T21:50+0300
2025-03-22T22:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий