በደቡብ ምዕራብ ኒጀር በተፈጸመ የሽብር ጥቃት ቢያንስ 44 ንፁሀን ሲገደሉ 13 ሰዎች መቁሰላቸው ተሰማ

ሰብስክራይብ
 በደቡብ ምዕራብ ኒጀር በተፈጸመ የሽብር ጥቃት ቢያንስ 44 ንፁሀን ሲገደሉ 13 ሰዎች መቁሰላቸው ተሰማ በታላቁ ሰሃራ *የእስላማዊ መንግሥት ታጣቂዎች የፈፅሙት ጥቃት በኮኮሩ ከተማ የፎንቢታ መስጂድ ምዕመናን ላይ ያነጣጠረ ነበር ተብሏል። የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሃመድ ቱምባ እንደገለጹት በጥቃቱ ከቆሰሉት 13 ሰዎች መካከል አራቱ በከባድ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ሚኒስቴሩ ድርጊቱን "የፈሪ እና ኢሰብዓዊ" ሲል ያወገዘ ሲሆን የፀረ-ሽብር ዘመቻውን እንደሚጠናከር አስረግጧል። የኒጀር መንግሥት ለጥቃቱ ተጎጂዎች ከቅዳሜ ጀምሮ የ72 ሰዓት ሀገራዊ የሐዘን ጊዜ አውጇል። በመላ ሀገሪቱ ባንዲራዎች በግማሽ ዝቅ ብለው የሚውለበለቡ ሲሆን ሕዝባዊ ዝግጅቶች ይቀነሳሉ። *ዳኢሽ ( አይኤስአይኤስ/አይኤስአይኤል/አይኤስ በመባልም ይታወቃል) በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ሀገራት የታገደ የሽብር ድርጅት ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0