ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነፃነት ያበረከተችውን አስተዋጽኦ አህጉሪቱን በማስተሳሰርም ትቀጥለዋለች ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ አንጋፋው የሥነ-ፅሑፍ ባለሙያ ገለጹ የዓድዋ ድል አፍሪካውያን ቅኝ ግዛትን እንዲታገሉ ያነሳሳ እንደነበር ያስታወሱት አንጋፋው የሥነ-ፅሑፍ ሰው አያልነህ ሙላቱ፤ ድሉ የኢትዮጵያን አንድነት ከማጠናከር ባለፈ ለፓን አፍሪካኒዝም መሠረት ጥሏል ብለዋል።"አፍሪካ ነፃነቷን ለማግኘት እነማንዴላ ሌሎችም ታላላቅ የአፍሪካ መሪዎች ስልጠና ወስደው ቅኝ ግዛትን የተዋጉት በኢትዮጵያ መሬት ላይ መጥተው ነው። ይሄ አንድ ትልቅ ኃይል ነው። መጨረሻ ላይም ያ ድል ተቀናጅቶ የአፍሪካ አንድነትን የፈጠረ ነው። የአፍሪካ አንድነትም መሠረት በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ መሆኑ ከዚህ ታሪካዊ እውነታ ጋር የተያያዘ ነው" ሲሉ ከ2ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ዘገቢ ተናግረዋል።አዲስ አበባ ውስጥ እየተካሄደ የሚገኘው የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል ረጅም ታሪክ ያለው ነው ያሉት ገጣሚና ጸሃፌ-ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፤ ኢትዮጵያ በተመሳሳይ አፍሪካን የሚያስተሳስሩ ውጥኖችን ትቅጥላለች ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። "ይሄ ዛሬ የምታየው የምስራቅ አፍሪካ የባህልና የጥበብ ፌስቲቫል መሠረት ያለው እንጂ ዝም ብሎ አሁን የተፈጠረ አይደለም። ረጅም ታሪክን ይዞ የተከበረ ነው። ትልቅ ሥራም ነው። ዛሬም ነገም ኢትዮጵያ ግንባር ቀደምነቷን፤ የአፍሪካ አስተባባሪነቷን ቀጥላ ከዚህ የበለጠ ደግሞ መላው አፍሪካን የሚያስተሳስር ፌስቲቫል ይጠበቃል" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነፃነት ያበረከተችውን አስተዋጽኦ አህጉሪቱን በማስተሳሰርም ትቀጥለዋለች ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ አንጋፋው የሥነ-ፅሑፍ ባለሙያ ገለጹ
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነፃነት ያበረከተችውን አስተዋጽኦ አህጉሪቱን በማስተሳሰርም ትቀጥለዋለች ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ አንጋፋው የሥነ-ፅሑፍ ባለሙያ ገለጹ
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነፃነት ያበረከተችውን አስተዋጽኦ አህጉሪቱን በማስተሳሰርም ትቀጥለዋለች ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ አንጋፋው የሥነ-ፅሑፍ ባለሙያ ገለጹ የዓድዋ ድል አፍሪካውያን ቅኝ ግዛትን እንዲታገሉ ያነሳሳ እንደነበር ያስታወሱት አንጋፋው... 21.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-21T20:54+0300
2025-03-21T20:54+0300
2025-03-21T21:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነፃነት ያበረከተችውን አስተዋጽኦ አህጉሪቱን በማስተሳሰርም ትቀጥለዋለች ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ አንጋፋው የሥነ-ፅሑፍ ባለሙያ ገለጹ
20:54 21.03.2025 (የተሻሻለ: 21:14 21.03.2025)
ሰብስክራይብ