ፍራንስ 24 በኮትዲቯር ዙሪያ ከሠራው "አድሎአዊ" ዜና ጋር ተያይዞ ማሰጠንቀቂያ ተሰጠው

ሰብስክራይብ
ፍራንስ 24 በኮትዲቯር ዙሪያ ከሠራው "አድሎአዊ" ዜና ጋር ተያይዞ ማሰጠንቀቂያ ተሰጠው የኮትዲቯር የኮሙኒኬሽን እና የኦዶቪዡዋል ባለስልጣን በሀገሪቱ ሕገ-ወጥ ስደት ዙሪያ የቀረበው ዘገባ “ጥልቀት የሌለው እና አድሏዊ” ነው ሲል ኮንኖታል። እንደ ባለስልጣኑ ገለፃ የተሠራው ዘጋቢ ፊልም የሀገሪቱ የሕገ-ወጥ ስደት ችግር የተፈጠረው ባልተመጣጠነ የኢኮኖሚ ዕድገት እና በመንግሥት ስንፍና እንደሆነ ይጠቁማል። ፍራንስ 24 በሪፖርቱ የኮትዲቯር ባለስልጣናትን አስተያየት ባለመካተቱም ተወቅሷል። ሪፖርቱ መንግሥት "ሕገ-ወጥ ስደትን አስመልክቶ እርምጃ ባለመወሰድ እና ጉዳዩን ችላ በማለት ሕዝቡ በድህነት እንዲኖር ፈቅዷል" የሚል አንደምታ ፈጥሯል ተብሏል። የኮትዲቯር የኮሙኒኬሽን እና የኦዶቪዡዋል ባለስልጣን የተሰበሰበውን መረጃ በተመለከተ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሚዲያውን ጠይቋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0