በሶማሊያ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የረመዳን ፆምን አስመልክቶ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አደረገ

ሰብስክራይብ
በሶማሊያ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የረመዳን ፆምን አስመልክቶ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አደረገወታደሮቹ በጌዶ ክልል ባርድሂር ከተማ ለሚገኙ ለችግር የተጋለጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች ስኳር፣ ፓስታ፣ ዱቄት፣ ዘይት እና ቴምር የመሳሰሉትን የምግብ አቅርቦቶች እንደለገሱ ተነግሯል።የሻለቃው ኮማንደር ኮሌነል ሞላ ሹመት ወታደሮቹ ለደህንነት እና ሰብዓዊ ድጋፍ ቁርጠኛ ናቸው ማለታቸውን የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ በማህበራዊ ትሥሥር ገፁ አስታውቋል። የባርድሂር ወረዳ ኮሚሽነር ኢስማኢል ሼክ አብዲ "ሰላምን ከማረጋገጥ በተጨማሪ ለሕብረተሰቡ የምታደርጉትን ሰብዓዊ ድጋፍ አሳይታችኋል። ላደረጋችሁት ወቅታዊ ድጋፍ በጣም እናመሰግናለን" ብለዋል።የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ልዑክ ከዚህ ቀደም ለአካባቢው ሆስፒታል የመድኃኒት እና የህክምና ቁሳቁስ እገዛ ማድረጉ ይታወሳል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0