የብሬቶን ዉድስ ተቆማት፣ ተመድ እና ሌሎችም ለአሁኗ አፍሪካ የሚመጥኑ አይደሉም ሲሉ አፍሪካዊ የኢኮኖሚ ባለሙያ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የብሬቶን ዉድስ ተቆማት፣ ተመድ እና ሌሎችም ለአሁኗ አፍሪካ የሚመጥኑ አይደሉም ሲሉ አፍሪካዊ የኢኮኖሚ ባለሙያ ተናገሩ "እነዚህ ተቋማት የአፍሪካ ሀገራት በቅኝ ግዛት በነበሩበት ወቅት የተቋቋሙ ናቸው። ባለፉት አስርት ዓመታት ጥቂት ማሻሻያዎች ቢያደርጉም፤ አብዛኛዎቹ ባለድርሻ አካላት ለራሳችው ጥቅም በሚመች መልኩ የገነቧቸው በመሆኑ አግባብነት የላቸውም" ሲሉ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማዕከል ፕሬዝዳንት ማቪስ ኦውሱ-ጂያምፊ ከ57ኛው የአፍሪካ የኢኮኖሚ ሚኒስትሮቸ ጉባኤ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ባለሙያዋ አክለውም የባለብዙ ወገን የልማት ባንኮች ለውጥ እንዲያደርጉ እንዲሁም በጠረጴዛው ዙርያ መቀመጫ ለማግኘት አፍሪካውያን የበለጠ ስልታዊ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል።ከፍተኛዎቹ ተበዳሪዎች አፍሪካውያን ናቸው ያሉት ማቪስ ኦውሱ-ጂያምፊ፤ ሆኖም እንደ ተበዳሪ አቋማቸውን የሚገልጹበት ሕብረት ሊፈጥሩ ይገባል ብለዋል።"የአፍሪካ ተበዳሪዎች ቡድን ሕብረት የምንፈጥርበት ጊዜ ላይ ነን። አንድ ላይ በመሰባሰብ ልምድ፣ እውቀት የምንለዋወጥበት እና አበዳሪዎቻችንን የምንጠይቅበት መድረክ ይሆናል። ትብብር መፍጠራችን እና መማማራችን በድርድር ወቅት ስህተቶቻችንን እንዳንደግም ይረዳናል" ሲሉም አክለዋል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0