በፑቲን-ትራምፕ ውይይት ዙሪያ በኋይት ሀውስ መግለጫ የተጠቀሱ ቁልፍ ነጥቦች፦

ሰብስክራይብ
በፑቲን-ትራምፕ ውይይት ዙሪያ በኋይት ሀውስ መግለጫ የተጠቀሱ ቁልፍ ነጥቦች፦ ▪ ሁለቱ መሪዎች በዩክሬን ሰላም እና የተኩስ ማቆም አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል። ▪ መሪዎቹ ወደ ሰላም የሚደረገው ሂደት በኃይል እና በመሠረተ ልማት ተኩስ አቁም እንዲጀመር ተስማምተዋል። ▪ ፕሬዝዳንቶቹ በጥቁር ባህር የማሪታይም የተኩስ አቁም ንግግር "በአፋጣኝ" በመካከለኛው ምስራቅ እንዲጀመር ተስማምተዋል። ▪ ፑቲን እና ትራምፕ በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል ያለው የተሻሻለ የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደፊት ትልቅ ጥቅም እንደሚኖረው መግባባት ላይ ደርሰዋል። ▪ የሩሲያ እና አሜሪካ መጪው ግንኙነት "ግዙፍ የኢኮኖሚ ስምምነቶችን" እና የጂኦፖለቲካዊ መረጋጋትን ያካትታል ብለዋል። ▪ መሪዎቹ የስትራቴጂክ መሳሪያዎች መበራከትን ማስቆም እንደሚያስፈልግ ተወያይተዋል። ▪ ሁለቱ መሪዎች ኢራን እስራኤልን ማጥፋት በምትችልበት አቋም ላይ በፍፁም መድረስ እንደሌለባት ሃሳብ ተለዋውጠዋል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0