ፕሬዝዳንት ፑቲን በሩሲያ የኢንዱስትሪ እና ሥራ ፈጣሪዎች ህብረት ኮንግረስ ላይ የሰጡት መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ፑቲን በሩሲያ የኢንዱስትሪ እና ሥራ ፈጣሪዎች ህብረት ኮንግረስ ላይ የሰጡት መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፡-ሙሉ ሉዓላዊነታቸውን ማረጋገጥ የሚችሉ ሀገራት ብቻ የውጭ ጫናዎችን ይቋቋማሉ፡፡ አብዛኞዎቹ የአውሮፓ ሀገራት ሉዓላዊነታቸውን በማጣታቸው ምክንያት የከፋ ኢኮኖሚያዊና የጸጥታ ችግር ተጋርጦባቸዋል።በዓለም ላይ አዲስ የኢኮኖሚ ፉክክር እየበረታ መጥቷል።28 ሺህ 595 ማዕቀቦች ሩሲያ ላይ ተጥለዋል።ማዕቀቦች ጊዜያዊ ወይም የአንድ ጊዜ እርምጃዎች ሳይሆኑ ሩሲያ ላይ ጫና መፈጥሪያ መንገዶች ናቸው። ማዕቀቡ ቢነሳም ምዕራቡ ዓለም ሞስኮን ለማሰናከል ሌላ መንገድ ይፈጥራል፡፡ የፀረ-ሩሲያ ማዕቀቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ነፃነትን ይጎዳሉ።ማዕቀቦች ለሩሲያ ኢኮኖሚ አቀጣጣይ ሆነዋል። የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች የምዕራባውያን ኩባንያዎችን መልቀቅ ተጠቅመው ገበያውን ተቆጣጥረዋል።የምዕራባውያን ኩባንያዎች ዳግም ወደ ሩሲያ መመለስን በተመለከተ፤ በሀገሪቱ ውስጥ ሥራቸውን የቀጠሉ ኩባንያዎች ቦታ እንደሚኖራችው የሩሲያው ፕሬዝዳንት ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ከሩሲያ ገበያ ወጥተው ንግዳቸው የተያዘባቸው ግን ዘግይተዋል ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0