ኬኒያ ከውዝፍ ዕዳ ጋር በተያያዘ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አዲስ የክፍያ ፕሮግራም ጠየቀች

ሰብስክራይብ
ኬኒያ ከውዝፍ ዕዳ ጋር በተያያዘ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አዲስ የክፍያ ፕሮግራም ጠየቀች የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ተልዕኮ ኃላፊ ሐይማኖት ተፈራ ኬኒያ አዲስ ፕሮግራም እንደጠየቀች አረጋግጠዋል። ሁለቱ ወገኖች በዘጠነኛው የተራዘመ የፈንድ አቅርቦት እና የተራዘመ የብድር አቅርቦት ፕሮግራሞች ግምገማ ላለመቀጠል በመስማማታቸው የ480 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ከጠረጴዛ ውጪ ሆኗል።እርምጃው የተወሰደው በከፍተኛ የዕዳ ክፍያ ምክንያት የኬንያ የበጀት-ፋይናንስ ክፍተት እየሰፋ በመጣበት ወቅት ነው። ኬኒያ ከአይኤምኤፍ ጋር ያላት የ3.6 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት መጋቢት 23 ያበቃል። ይህ ስምምነት ከኮቪድ-19 በኋላ የሀገሪቱን የማገገም ሂደት ለመደገፍ አልሞ የነበረ ቢሆንም የፊስካል ጫናዎችን ማቃለል አልቻለም። እ.አ.አ 2023 በፀደቀው የተለየ የማቋቋማያ እና የዘላቂነት ፈንድ ከተመደበው 541.3 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 180.4 ሚሊዮን ዶላሩ ተከፍሏል።የአዲሱ ፕሮግራም ዝርዝር ብድር ወይም ብድር ያልሆኑ ውሎችን ሊያካትት ይችላል ተብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0