ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲስ የልማት ባንክ አባል ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎት አላት ሲሉ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ድርበው ተናገሩ

ሰብስክራይብ
 ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲስ የልማት ባንክ አባል ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎት አላት ሲሉ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ድርበው ተናገሩ አምባሳደሩ ከባንኩ ፕሬዝዳንት ዲልማ ሮሴፍ ጋር በትላንትናው ዕለት ሻንጋይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ውይይት አድርገዋል። የውይይቱ ትኩረት ኢትዮጵያ ባቀረበችው የባንኩ አባልነት ጥያቄ ላይ እንደነበር ቤጂንግ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።አምባሳደሩ ኢትዮጵያ ባከናወነችው መጠነ ሰፊ የዲፕሎማሲ ሥራ ምክንያት በርካታ የባንኩ አባል ሀገራት የአባልነት ጥያቄዋን መደገፋቸውን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቷ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ጥያቄ ለአባል ሀገራቱ እንደሚያስረዱ አረጋግጠዋል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0