🪖 የአውሮፓ ሀገራት ከ10 ሺህ በላይ ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን በዩክሬን ለማሠማራት እያቀዱ መሆኑ ተሰማ

ሰብስክራይብ
🪖 የአውሮፓ ሀገራት ከ10 ሺህ በላይ ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን በዩክሬን ለማሠማራት እያቀዱ መሆኑ ተሰማ ታይምስ ጋዜጣ ያጣቀሰው የብሪታኒያ ወታደራዊ ምንጭ  "ብዙ ሃገራት ሠራዊት በማቅረብ እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስብስብ ደግሞ በሌላ መንገድ በሚያደርጉት አስተዋጽኦ ትልቅ ኃይል ይሆናል” ብሏል፡፡ ምንም እንኳን ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ ከፍተኛ ቁጥር ወታደሮችን ለማቅረብ ቢያቅዱም፤ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ተጨማሪ ሀገራት ወደ ዩክሬን ወታደር እንዲያሠማሩ በማሳመን በኩል እንደተሳካላቸው ተነግሯል።ሪፖርቱ ለሚሠማራው የአውሮፓ ተልዕኮ ከ35 በላይ ሀገራት የመሣርያ፣ የቁሳቁስ፣ የቴክኒክ እና የመረጃ ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብተዋል ብሏል።   ብሪታኒያ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿ "ለዓመታት" በዩክሬን የሰላም ማስከበር ተልዕኮ አካል ሆነው እንዲያገለግሉ ፍቃደኛ እንደሆነች ዘ ታይምስ በዘገባው አትቷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0