ሩዋንዳ ከቢልጅየም ጋር የነበራትን  ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት አቋረጠች

ሰብስክራይብ
ሩዋንዳ ከቢልጅየም ጋር የነበራትን  ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት አቋረጠች "ቤልጅየም አሁን ካለው የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭትም ሆነ ከዛ በፊት ሩዋንዳን በተደጋጋሚ ጎድታለች፤ በተለይም ቤልጅየም ሩዋንዳ ላይ ጉዳት በማድረስ ረጅም እና ደም አፋሳሽ ታሪክ አላት” ሲል የሩዋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ተነቧል። ሩዋንዳ ሁሉም የቤልጅየም ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡም ትዕዛዝ አስተላልፋለች።ቤልጅየም "በተለያዩ መንገዶች ከሩዋንዳ በተቃራኒ ትቆማለች እንዲሁም ሀገሪቱን እና ቀጣናውን ለማተራመስ ውሸት እና ተጽእኖዋን ተጥቀማ ሩዋንዳ ላይ አሉታዊ አመለካከት እንዲዳብር አድርጋለች" ሲል ሚንስቴር መስርያ ቤቱ ገልጿል።ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በኪጋሊ ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር "ቤልጂየማውያን ባለፉት 30 ዓመታት ሩዋንዳን አፍርሰዋል፣ ሩዋንዳውያንን ገድለዋል" ያሉ ሲሆን፤ ብራሰልስ በምስራቃዊ ኮንጎ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ሩዋንዳ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጫና እያሳደረች ነው በማለትም ከሰዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን።
አዳዲስ ዜናዎች
0