ኤል ሳልቫዶር ከአሜሪካ የተባረሩ የመጀመሪያ ዙር የቬንዙዌላ ወንጀለኞችን እንደተቀበለች ፕሬዝዳንቷ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ኤል ሳልቫዶር ከአሜሪካ የተባረሩ የመጀመሪያ ዙር የቬንዙዌላ ወንጀለኞችን እንደተቀበለች ፕሬዝዳንቷ ተናገሩ "የቬንዙዌላ የወንጀል ቡድን የትሬን ደ አራጓ የመጀመሪያዎቹ 238 አባላት ዛሬ ወደ ሀገራችን ገብተዋል። ለአንድ ዓመት (ሊታደስ ለሚችል) ቆይታ ወዲያውኑ ወደ ሽብርተኞች ማቆያ ማዕከል ተዛውረዋል" ሲሉ የኤል ሳልቫዶር ፕሬዝዳንት ናይብ ቡኬል ገልፀዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም በአሜሪካ የተያዙና በሳልቫዶር የፍትሕ አካላት የሚፈለጉ 23 የኤምኤስ-13 የወንጀል ቡድን አባላት በአውሮፕላኑ ከተጓጓዙት ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል። በየካቲት ወር ኤል ሳልቫዶር 40 ሺህ እስረኞችን መያዝ በሚችለው ግዙፍ የሽብርተኞች ማቆያ ማዕከል የአሜሪካ ዜጎችን ጨምሮ ወንጀለኞችን በክፍያ ለማቆየት ሀሳብ አቅርባ የነበረ ሲሆን፤ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ዩናይትድ ስቴትስ ሀሳቡን እንደምታጤን ጠቁመው ነበር።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0