የጤና ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን መሥራት እንደሚገባቸው አሳሰበበጤና ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬሕይወት አበበ የተመራ ቡድን በኢትዮጵያ የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎች አንዱ የሆነውን ሂውማንዌል ፋርማሲዩቲካል ኢትዮጵያን ጎብኝቷል። በጉብኝቱ የሀገር ውስጥ የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎች በአቅርቦት ያላቸው ድርሻ እየጨመረ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታዋ ፍሬሕይወት አበበ ጠቁመዋል። ይህም የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል ወሳኝ እንደሆነ የገለጹት ባለስልጣኗ፤ ምርቶቹ በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥራት ተወዳዳሪ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል። በዚህ ረገድ ጤና ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንና ለዚህም ስኬት የሀገር ውስጥ የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪ ልማት ፎረም በማቋቋም ወደ ሥራ እንደተገባም ተገልጿል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የጤና ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን መሥራት እንደሚገባቸው አሳሰበ
የጤና ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን መሥራት እንደሚገባቸው አሳሰበ
Sputnik አፍሪካ
የጤና ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን መሥራት እንደሚገባቸው አሳሰበበጤና ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬሕይወት አበበ የተመራ ቡድን በኢትዮጵያ የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎች አንዱ የሆነውን... 16.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-16T20:12+0300
2025-03-16T20:12+0300
2025-03-16T20:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የጤና ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን መሥራት እንደሚገባቸው አሳሰበ
20:12 16.03.2025 (የተሻሻለ: 20:44 16.03.2025)
ሰብስክራይብ