ሩቢዮ እና ላቭሮቭ በሩሲያ እና አሜሪካ ቀጣይ ግኑኝነት ዙርያ በስልክ ተወያዩ

ሰብስክራይብ
 ሩቢዮ እና ላቭሮቭ በሩሲያ እና አሜሪካ ቀጣይ ግኑኝነት ዙርያ በስልክ ተወያዩ "የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ…በአሜሪካ እና ሩሲያ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደነበረበት ለመመለስ ጥረታቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል" ሲል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ገልጿል።የአሜሪካ እና ዩክሬን ልዑካን ማክሰኞ በሳዑዲ አረቢያ ተገናኝተው ሊራዘም የሚችል የ30 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ዩክሬን በእቅዱ መስማማቷን ተከትሎ አሜሪካ ለኪዬቭ የምታደርገውን የመረጃ እና ወታደራዊ ድጋፍ ዳግም ጀምራለች። የክሬምሊን አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ የተኩስ አቁሙ ለዩክሬን ጊዜያዊ እረፍት የሚሰጥ ብቻ ነው በማለት ውድቅ አድርገውታል። ስምምነቱ የሩሲያን ጥቅም ግምት ውስጥ ማስገባት አለበትም ብለዋል። ሩሲያ ከጥቅሟ ጋር የተጣጣመ ዘላቂ የሰላም ስምምነት እንደምትሻ የምትገልጽ ሲሆን፤ ቭላድሚር ፑቲን በተኩስ አቁም ስምምነቱ ዙርያ የሩሲያን ይፋዊ አቋም በቅርቡ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በስልክ ወይይቱ ላይ ሩቢዮ አሜሪካ በየመን አንሳር አላህ ንቅናቄ (ሁቲዎች) ላይ ያካሄደችውን ዘመቻ በተመለከተ ለላቭሮቭ መረጃ አጋርተዋል። "በኢራን በሚደገፉት ሁቲዎች ላይ የአሜሪካ ወታደራዊ መከላከያ እርምጃዎችን በተመለከተ ለሩሲያ ወቅታዊ መረጃ በመስጠት፤ ሁቲዎች በቀይ ባህር የአሜሪካ ወታደራዊ እና የንግድ ማመላለሻ መርከቦች ላይ የሚደረጉትን ጥቃት አሜሪካ እንደማትታገስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አፅንኦት ሰጥተዋል" ሲል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0