የአሜሪካ ጦር ጄቶች በሰሜናዊ የመን በሚገኙ የኃይል ጣቢያዎች ላይ ድብደባ ፈጸሙ የየመን የቴሌቭዥን ጣቢያ አል-ማሲራህ እንደዘገበው አሜሪካ በሰሜናዊ የመን ሰአዳ ግዛት ዳህያን ከተማ የሚገኘውን የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በመምታቷ በከተማዋ እና አካባቢው ኃይል ተቋርጧል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በቅርቡ በአሸባሪነት በፈረጀችው እና ሰሜናዊ የመንን በሚቆጣጠረው የሺዓ ወታደራዊ-ፖለቲካዊ ንቅናቄ አንሳር አላህ (ሁቲዎች) ላይ ወሳኝ እርምጃ እንዲወሰድ ባስተላለፉት ትዕዛዝ መሠረት ነው ዩናይትድ ስቴትስ የመን ላይ የአየር ጥቃቱን ያካሄደችው። "የአሜሪካ ተዋጊ ጄቶች በራዳ ክልል ከአንሳር አላህ ንቅናቄ (ሁቲስ) ጋር ግኑኝነት ያለውን የአል-ኩሲር ካምፕ እና በአል-ኩራይሽያ ክልል የሚገኘውን አል-ኩራይሽያ የቴክኒክ ኢንስቲትዩት ጨምሮ ስምንት ጥቃቶችን በአል ባይዳ ግዛት ፈፅመዋል" ሲሉ አንድ የየመን ምንጭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። የአሜሪካ ተዋጊ አውሮፕላኖች ከዋና ከተማይቱ ሰነዓ በስተደቡብ በምትገኘው ዳማር ግዛት ላይ ሁለት ጥቃት አድርሰዋል። የጥቃቶቹ ዒላማ በዳማር ከተማ የሚገኘው የፖሊስ ቢሮ እና ወርክሾፕ እንደነበር ምንጩ አክለው ገልጸዋል። ሁቲዎች እስራኤል የካቲት 23 ቀን ወደ ጋዛ በሚገባው የሰብዓዊ እርዳታ ላይ እገዳ መጣሏን ተከትሎ በቀይ እና አረብ ባህር፣ በባብ አል-ማንደብ ሰርጥ እና በኤደን ባህረ ሰላጤ በሚንቀሳቀሱ የእስራኤል መርከቦች ላይ ወታደራዊ እርምጃ በድጋሚ እንደሚጀምሩ ቀደም ብለው አስታውቀዋል። ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኙት ምስሎች አሜሪካ በየመን ያካሄደችውን ጥቃት ያሳያሉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የአሜሪካ ጦር ጄቶች በሰሜናዊ የመን በሚገኙ የኃይል ጣቢያዎች ላይ ድብደባ ፈጸሙ
የአሜሪካ ጦር ጄቶች በሰሜናዊ የመን በሚገኙ የኃይል ጣቢያዎች ላይ ድብደባ ፈጸሙ
Sputnik አፍሪካ
የአሜሪካ ጦር ጄቶች በሰሜናዊ የመን በሚገኙ የኃይል ጣቢያዎች ላይ ድብደባ ፈጸሙ የየመን የቴሌቭዥን ጣቢያ አል-ማሲራህ እንደዘገበው አሜሪካ በሰሜናዊ የመን ሰአዳ ግዛት ዳህያን ከተማ የሚገኘውን የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በመምታቷ በከተማዋ እና አካባቢው... 16.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-16T15:14+0300
2025-03-16T15:14+0300
2025-03-16T15:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የአሜሪካ ጦር ጄቶች በሰሜናዊ የመን በሚገኙ የኃይል ጣቢያዎች ላይ ድብደባ ፈጸሙ
15:14 16.03.2025 (የተሻሻለ: 15:44 16.03.2025)
ሰብስክራይብ