‍‍ ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ተካሄደ

ሰብስክራይብ
‍‍ ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ተካሄደ በታላቁ ሩጫ ኢትዮጵያ እና አጋሮቹ ትብበር በተዘጋጀው ውድድር ላይ ከ16 ሺህ በላይ ሴቶች ተሳትፈዋል። ውድድሩ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በማስመልከት ''ሁሉም መብቶች ለመላው ሴቶች" በሚል መሪ ቃል ተካሄዷል። በኦሊምፒክ የድርብ ሜዳሊያ አሸናፊና የውድድሩ አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋር ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ፤ "ቅድሚያ ለሴቶች ውድድር ተምሳሌት የሆኑ ሴቶችን በማምጣትና ውድድሩ ላይ እንዲገኙ በማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ ነው። በተለይም ለአትሌቶች መውጫ ስለሆነ ትልቅና ለሴቶች አስተዋጽኦ ያለው ውድድር ነው" ስትል ተናግራለች። ውድድሩ እየሠራ ያለውን የግንዛቤ ለውጥ ለማስፋት በቀጣይ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ጭምር ተወዳዳሪዎች እንዲሳተፉ ሥራዎች ይሠራሉ ብላለች። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0