አሜሪካ ክርስቲያኖች ናይጄሪያ ውስጥ መሳደድ እየደረሰባቸው ነው ስትል ያቀረበችውን ክስ አቡጃ ውድቅ አደረገች

ሰብስክራይብ
አሜሪካ ክርስቲያኖች ናይጄሪያ ውስጥ መሳደድ እየደረሰባቸው ነው ስትል ያቀረበችውን ክስ አቡጃ ውድቅ አደረገች ምላሹ የተሰጠው የሪፐብሊካን ኮንግረስ አባል ክሪስ ስሚዝ ናይጄሪያ ውስጥ በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በማንሳት ሀገሪቱ በተለየ አሳሳቢ ሀገር ተብላ እንድትሰየም ሀሳብ ካቀረቡ በኋላ ነው። ስያሜው በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚጸደቅ ከሆነ ናይጄሪያ ላይ ማዕቀብ ሊጣል ይችላል። ናይጄሪያ በ2020 በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ወቅት ስያሜው ተሰጥቷት የነበረ ሲሆን፤ በ2021 በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከዝርዝሩ ወጥታለች። የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አርብ እለት በሰጠው መግለጫ በሀገሪቱ ያለው ግጭት እና አለመረጋጋት ከሐይማኖት አድልዎ ጋር የተገናኘ አይደለም ብሏል። "በአብዛኛው ሙስሊሞች በሚገኙበት ሰሜን ናይጄሪያ ክፍል የሚታየው አመጽ እና ውንብድና በተለየ የትኛውም እምነት ወይም ሐይማኖት ተከታይ ላይ የተነጣጠረ አይደለም" ሲል ሚኒስቴሩ ገልጿል። በተጨማሪም ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በናይጄሪያ ክርስቲያኖች እየተለዩ ይገደላሉ የሚሉ “የተሳሳቱ እና አሳች መረጃዎች መስፋፋታቸው” እንዳሳሰበው አስታውቋል። በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆነችው ናይጄሪያ በአብዛኛው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሚኖሩበት ደቡብ እና ሙስሊሞች በሚበዙበት ሰሜን መካከል እኩል ተከፍላለች። በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0